‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤

‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤

ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀሎችህ የሰማይ ደመና ቢደርሱና ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ የአደም ልጅ ሆይ! ምድርን ሊሞላ በቀረበ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣ ከዚያም በኔ አንድንም ሳታጋራብኝ ብትገናኘኝ እኔም ምድርን ሊሞላ በቀረበ ምህረት ወዳንተ እመጣለሁ።›"»

[ሐሰን ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል። - Ad-Daarimi]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሐዲሠል ቁድስ ውስጥ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: የአደም ልጅ ሆይ! እኔን በመለመን፣ እዝነቴን በመከጀልና ተስፋ ባለመቁረጥ ላይ እስከዘወተርክ ድረስ ይህ ወንጀልህና ሀጢዐትህ ከትላልቅ ወንጀሎች ቢሆንም እንኳ እሸሽገዋለሁ፣ ምንም ሳይመስለኝም አብሰዋለሁ። የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀልህ በሰማይና በምድር መካከል ያለውን በሚሞላና ምድርንም ከጫፍ እስከጫፍ በሚደርስና ጎኖቿን በሚያጠቃልል መልኩ ቢበዛ ከዚያም ምህረት ብትጠይቀኝ ብዛቱ ምንም ሳይመስለኝ ሁሉንም ላንተ አብሰዋለሁም እምርሃለሁኝም። የአደም ልጅ ሆይ! አንተ ከሞት በኋላ ወደኔ ምድርን በሚሞላ ወንጀሎችና ሀጢዐቶች ብትመጣ በብቸኝነቴ አምልከሀኝ በኔ አንድንም ሳታጋራ ከሆነ የሞትከው እነዚህን ወንጀሎችህንና ሀጢዐቶችህን ምድርን በሚሞላ ምህረት እገናኛቸዋለሁ። እኔ ምህረተ ሰፊ ነኝና። ከሺርክ በስተቀርም ሁሉንም ወንጀሎችህን እምራለሁ።

فوائد الحديث

የአላህ እዝነትና ምህረት ሰፊ መሆኑንና ደረጃውንም እንረዳለን።

የተውሒድን ትሩፋት እንረዳለን። አላህ ለተውሒድ ሰዎች ወንጀልና ሀጢዐታቸውን ይምራል።

የሺርክን አደጋና አላህ አጋርያንን እንደማይምርም እንረዳለን።

ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ወንጀልን የሚያስምሩትን ሶስት ሰበቦች አጠቃልሏል። የመጀመሪያው: ከመከጀል ጋር ዱዓ ማድረግ ነው። ሁለተኛ: ምህረትን መጠየቅና ንስሀን መፈለግ ነው። ሶስተኛ: በተውሒድ ላይ መሞት ነው።»

ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጌታቸው ከሚያወሩት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። "ሐዲሠል ቁድሲይ" ወይም "ሐዲሠል ኢላሂይ" በመባልም ይጠራል። ይህም ማለት ቃሉም መልዕክቱም ከአላህ የሆነና ነገር ግን በማንበቡ እንደማምለክ፣ ለርሱ ዉዱእ ማድረግና የርሱን አምሳያ አምጡ ብሎ አላህ መገዳደሩን የመሰሉ የቁርአን መለዮዎች የሌለው ነው።

ወንጀሎች ሶስት አይነቶች ናቸው: የመጀመሪያው: በአላህ ማጋራት ነው። ይህም አላህ የማይምረው ወንጀል ነው። አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ ብሏል {እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ።} ሁለተኛው: አንድ ባሪያ በርሱና በጌታው መካከል ባለው ጉዳይ በወንጀልና ሀጢዐት ነፍሱን መበደሉ ነው። ይህንንም አላህ ከሻ የሚያልፈውና ይቅር የሚለው ነው። ሶስተኛ: አላህ አንዳችም የማይተወው ወንጀል ነው። እርሱም: ባሮች አንዳቸው አንዳቸውን መበደላቸው ነው። ይህንንም የግድ የማመሳሰል ፍርድ ተፈፃሚ ይሆንበታል።

التصنيفات

አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል, ተውበት