إعدادات العرض
ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ!
ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ!
ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ካለውና ከጠራው አላህ ባወሩት (ሐዲሠል ቁድሲይ) አላህ እንዲህ ብሏል: "ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ! ባሮቼ ሆይ! ከመራሁት በስተቀር ሁላችሁም ጠማማ ናችሁና ምራቻን ከኔ ጠይቁ እመራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! ካበላሁት በስተቀር ሁላችሁም ረሀብተኞች ናችሁና መብልን ከኔ ጠይቁ እመግባችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እኔ ካለበስኩት በስተቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ጠይቁ አለብሳችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ በሌሊትም ሆነ በቀን ትሳሳታላችሁ። እኔ ደግሞ ሁሉንም ወንጀሎችን እምራለሁ። ስለሆነም ምህረትን ከኔ ፈልጉ እምራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ እኔን ጉዳትን ልትጎዱኝ አትችሉም። ጥቅምን ልትጠቅሙኝ ዘንድም አትችሉም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም ከናንተ መካከል እንደሚገኝ አንድ እጅግ አላህን ፈሪ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይጨምርም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም እንደ አንድ እጅግ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰው ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም በአንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ቢቆሙና ቢጠይቁኝ ለእያንዳንዱም የጠየቀኝን ብሰጠው መርፌ ባህር የገባች ጊዜ እንደምትቀንሰው ያህል ካልሆነ በቀር ይህ (መስጠቴ) እኔ ዘንድ ካለው (ሀብት) ምንም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ይህቺ ስራችሁ ናት ለናንተ አስቀምጥላችኋለሁ ከዚያም እራሷን እመነዳችኋለሁ። ምንዳውን መልካም ሆኖ ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከዛ ውጪ ሆኖ ያገኘ ግን ከነፍሱ በስተቀር ማንንም እንዳይወቅስ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili فارسی မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Malagasy тоҷикӣ Oromoo Wolof Български Українська Azərbaycan ქართული bm Lingala Македонскиالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በደልን በነፍሱ ላይ እርም እንዳደረገና አንዱ አንዱን እንዳይበድል በደልን በፍጡራኑ መካከልም እርም እንዳደረገው መናገሩን አብራሩ። ሁሉም ፍጡራን በአላህ መምራትና መግጠም ካልሆነ በቀር ከእውነተኛው መንገድ የጠመሙ ናቸው። መመራትን ከአላህ የጠየቀ ሰው አላህም ይገጥመዋል ይመራዋልም። ፍጡራን በሁሉም ጉዳዮቻቸው ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸው። አላህን የጠየቀን ሰው አላህም ጉዳዩን ይፈፅምለታል ይበቃዋልም። ፍጡራን ሌት ተቀን ወንጀል ይፈፅማሉ። አላህ ደግሞ ባሪያው ምህረትን በሚጠይቀው ወቅት ይሸሽገዋልም ያልፈዋልም። ፍጡራን አላህን አንዳችም ሊጎዱም ወይም ሊጠቅሙ አይችሉም። ፍጡራን ሁሉ እንደ አንድ አላህን እጅግ የሚፈራ ቀልብ ያለው ግለሰብ ቢሆኑ ፍራቻቸው በአላህ ንግስና ላይ አትጨምርም። ሁሉም እንደ አንድ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑም ጥመታቸው በንግስናው ላይ አንዳችም አይቀንስም። ምክንያቱም ደካሞችና ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸውና። በሁሉም ሁኔታ፣ ዘመንና ስፍራ ወደርሱ ፈላጊዎች ናቸው። የተብቃቃም እሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ሰዉም ጋኔኑም ከመጀመሪያቸው እስከመጨረሻቸው አላህን ለመጠየቅ በአንድ ስፍራ ላይ ቢቆሙና ከነርሱም ለእያንዳንዱ ሁሉ የጠየቀውን ቢሰጥ ይህ መስጠቱ አላህ ዘንድ ካለው አንዳችም አይቀንስም። ልክ እንደ መርፌ ባህር ውስጥ ገብታ ብትወጣ ባህሩ በዚህ አንዳችም እንደማይቀነሰው ማለት ነው። ይህም የሆነው ከተሟላው ሀብቱ አንፃር ነው። ጥራት ተገባው! ጥራት የተገባው አላህ የባሮችን ስራዎች ይጠብቃልም ያስቀምጣልም። ከዚያም እሷኑ የትንሳኤ ቀን ይመነዳቸዋል። የስራውን ምንዳ መልካም ሆኖ ያገኘው ሰው አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ስለገጠመው አላህን ያመስግን። የስራውን ምንዳ ከዚህ ውጪ ሆኖ ያገኘ ሰውም ወደ ክስረት የመራችውን በመጥፎ የምታዘው ነፍሱን እንጂ ሌላን እንዳይወቅስ።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚዘግቡት ሐዲሦች መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድስ ወይም ሓዲሠል ኢላሂይ በመባልም ይጠራል። ይህም ቃሉም ሆነ መልዕክቱ ከአላህ የሆነ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ የቁርአን መለዮች የሉትም። ለምሳሌ: - በማንበቡ (ሓሰና የሚያስገኝ) አምልኮን መፈፀም፣ ለሱ ጦሀራ ማድረግ ፣ የሱን አምሳያ ከቻላቹ አምጡ የተባለለት ተዓምራዊነቱና ሌሎችም ቁርአን የተለየበት መለዮዎች ይጠቀሳሉ።
ባሮች የሚጎናፀፉት እውቀትና መመራት በአላህ መምራትና ማሳወቅ ነው።
አንድ ባሪያ የሚያገኘው መልካም ነገር በአላህ ችሮታ ነው። የሚያገኘው መጥፎ ነገር ግን በነፍሱና በስሜቱ ሳቢያ ነው።
መልካምን የሰራ በአላህ መግጠም ነው። የአላህ መመንዳትም ከአላህ የሆነ ችሮታ ስለሆነ ምስጋናው ለአሏህ ነው። መጥፎን የሰራ ግን ከነፍሱ በቀር ማንንም እንዳይወቅስ።