إعدادات العرض
ዐቂዳ (እምነት)
ዐቂዳ (እምነት)
2- በአይሁድ እና ክርስቲያኖች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ ! የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው ያዙ።
4- እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'
5- እኔ ከናንተ መካከል ፍፁም ወዳጅ ከመያዝ ወደ አላህ እጥራራለሁ። ምክንያቱም የላቀው አሏህ ኢብራሂምን ፍፁም ወዳጅ
6- ‹አላህ ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›
7- 'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'
8- በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
9- ‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›
13- የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'
14- በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።
15- በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።
16- ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።
18- ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።
19- አላህ ለሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።
22- አላህ ወደ ቅርፃችሁና ገንዘቦቻችሁ አይመለከትም ነገር ግን ወደ ልቦቻችሁና ስራዎቻችሁ ይመለከታል።
24- ‹በዚህ በመመሪያችን ውስጥ ከርሱ (ከትእዛዛችን) የሌለን አዲስ ነገር የፈጠረ ሰው እርሱ (የፈጠረው አዲስ ነገር) ተመላሽ ነው።
25- ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ!
27- ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር
28- ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።
30- ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።
31- የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።
32- ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም።
33- 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!
35- 'የገድ ተግባርን የፈፀመ ወይም ለሱ የተፈፀመለት፣ ወይም የጠነቆለ ወይም ያስጠነቆለ፣ ወይም የደገመ ወይም ያስደገመ፣
36- ሩቅ አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።
37- የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'
39- በግመል አንገት ላይ (የታሰረ) የቀስት ገመድ ወይም ገመድ የተቆረጠ ቢሆን እንጂ ምንም እንዳይቀር!'
40- 'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'
41- ለአዛኞች አዛኙ ጌታ ያዝንላቸዋል። ለምድር ነዋሪዎች እዘኑላቸው በሰማይ ያለው (አላህ) ያዝንላቹሀል።
45- የላቀውና ከፍ ያለው ጌታችን በሁሉም ሌሊት የመጨረሻ ሲሶ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል።
46- 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'
47- እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡ
51- እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና
53- አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ ወደ አንዱ በአልጋው ላይ እንደተደገፈ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው
55- በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
57- የትንሳኤ ቀን አላህ ከፍጡራኖች ከኔ ተከታዮች መካከል አንድ ሰው ይመርጣል
58- አላህ ጀነትና እሳትን እንደፈጠረ ጂብሪልን ዐለይሂ ሰላም
59- አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል
61- 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'
62- 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'
63- 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።
64- የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።
67- አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል።
72- አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።
73- ከናንተ በፊት የነበሩትን (ሕዝቦች) ጎዳና ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ።
74- ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።
77- 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።
101- በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
102- ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'
104- የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።
105- የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር!
108- ድሃ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁን?
111- 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።
116- መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።
119- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
121- ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።
125- ።" አሉ።
126- ጌታችሁ ምን እንዳለ ታውቃላችሁን?" ሰሓቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ" አሉ። እርሳቸውም አላህ እንዲህ አለ፦ "ከባሮቼ በኔ ያመነም የካደም ሆኖ ያነጋ አለ
128- የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
130- አላህ አማኝን አንድም መልካም ሥራውን አይበድለውም በዱንያ በሷ ምክንያት (መልካም ነገር) ሲሰጠው በአኺራም በሷ ምክንያት ይመነዳዋል
131- ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።
132- የሙናፊቅ ምሳሌው በሁለት (የፍየል) መንጎች መካከል እንደዋለለች ፍየል ነው። አንድ ጊዜ ወደ አንዱ ሌላ ጊዜም ወደ ሌላኛው ትሄዳለች።
133- ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።
135- አንድ ሰው በአንድ ሰው ቀብር በኩል እያለፈ 'ዋ ምኞቴ ምናለ በርሱ ስፍራ ላይ እኔ በነበርኩ!' እስኪል ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
136- አይሁዶችን ሳትዋጉና ከኋላው አንድ አይሁድ የተደበቀበት ድንጋይ ሙስሊሙ ሆይ! ይህ አይሁድ ከኋላዬ አለ ግደለው ሳይል ሰዓቲቱ አትቆምም።
138- ፀሀይ በመግቢያዋ እስክትወጣ ድረስ ሰዓቲቱ አትቆምም። ከመግቢያዋ የወጣችና ሰዎች የተመለከቷት ጊዜ ሁሉም ያምናሉ
139- ዘመኑ እስኪጣበብ ድረስ ሰአቲቱ አትቆምም።
140- 'አላህ ምድርን በጭብጡ ያደርጋል፤ ሰማያትንም በቀኝ እጁ ይጠቀልልና ከዚያም ‹እኔ ነኝ ንጉሱ! የምድር ነገስታት የት አሉ?!› ይላል።'
141- የሐውዴ ( ኩሬ ስፋቱ) አንድ ወር ያስኬዳል ፤ ውኃው ከወተት የነጣ፣ ሽታው ከሚስክ እጅግ የሚያውድ
143- የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! መጠጫ እቃው ከሰማይ ከዋክብት ቁጥር የበዛ ነው።
144- ሞት በቡራቡሬ ሙክት ተመስሎ ተይዞ ይመጣል
145- የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።
147- ስንፍናና ጮሌነት ወይም ጮሌነትና ስንፍና ሳይቀር ሁሉ ነገር በአላህ ውሳኔ ነው።
148- አላህ አንድ ባሪያ በአንድ ቦታ እንዲሞት የወሰነ ጊዜ ወደዚያ ስፍራ የሚሄድበትን ምክንያት ያደርግለታል።
149- እኔ የበኑ ሰዕድ ቢን በክር ወንድም ዲማም ቢን ሠዕለባህ ነኝ።" አላቸው።
150- ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አንድ ነገር ካወሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "ይህ የሚከሰተውም ዕውቀት ሊጠፋ የቀረበ ጊዜ ነው።
151- የመጽሐፍ ባለቤቶች (በሚተረጉሙላችሁ) አትመኑዋቸውም አታስተባብሏቸውም {በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርአን) አመንን………} በሉ።
152- ቁርኣን የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አርባ ዓመታቸው ላይ ሳሉ ወረደ
153- አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።
154- ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?
155- ላ ኢላሀ ኢለላህ በል የትንሳኤ ቀን ላንተ በርሱ እመሰክርልሀለሁ
156- የምትናገረውና የምትጣራበት ጉዳይ መልካም ነው። ለሰራነው ፀያፍ ተግባር ማስማሪያ እንዳለው እንደው ብትነግረን?
157- 'ወደርሱ ሂድና አንተ ከእሳት ሰዎች ሳትሆን ከጀነት ሰዎች ነህ በለው።' አሉት ሰውየውም ታላቅ የብስራት ዜና ይዞ በድጋሚ (ወደ ሣቢት) ተመለሰ።
158- {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።}
159- በመጨረሻዎቹ ሕዝቦቼ (ኡመቴ) ውስጥ እናንተም ሆነ አባቶቻችሁ ያልሰማችሁትን የሚነግሯችሁ ሰዎች ይመጣሉ። አደራችሁን አደራችሁን ተጠንቀቋቸው።
160- ጻፍ! ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ አንደበት እውነት እንጂ አይወጣም።'
161- ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ።
162- ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!
163- በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖት እና የነብዩ ሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።
165- መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።