'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።

'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'እንደነዚህ ልክ ወርውሩ!' አሉ። ቀጥለውም 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ፣ ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ኢብኑ ዓባስ (ረdiየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመሰናበቻ ሐጅ ወቅት የእርድ ቀን ጀምረተል ዐቀባ ንጋት ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እንደነበረ ተናገሩ። የሚወረውሩት ጠጠር እንዲለቅምላቸው አዘዙት። እርሱም ሰባት ጠጠሮች ለቀመላቸው። እያንዳንዱም ጠጠር የሽንብራ ወይም የለውዝ ፍሬ መጠን ነበር ያላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእጃቸው ላይ አኑረውት ጠጠሮቹን መደፋቸው ላይ እያንከባለሉ እንዲህ አሉ: የምትወረውሩት ጠጠር በዚህ ልክ ይሁን። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ወሰን ከማለፍና ከማክረር አስጠነቀቁ። የቀደሙ ህዝቦችን ያጠፋው ወሰን ማለፍና በሃይማኖት ላይ ከልክ በላይ ማክረር መሆኑንም ተናገሩ።

فوائد الحديث

በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ መከልከሉንና ፍፃሜው የከፋ መሆኑን እንዲሁም ለጥፋትም ምክንያት መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።

ከወደቁበት ስህተት ለመራቅ ሲባል ከቀደሙን ህዝቦች ትምህርት መውሰድ ተገቢ መሆኑን እንረዳለን።

ሱናን በመከተል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

የጃሂሊያ ጉዳዮች