የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'

የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የኮኮብ እውቀትን (በትንሹም) የቀሰመ ሰው ከፊልን ጥንቆላ ቀስሟል። (የኮኮብ እውቀት መቅሰሙን) በጨመረ ቁጥር (ጥንቆላውም) ይጨምራል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

የኮኮብ እውቀትን፣ የኮኮቦች እንቅስቃሴ፣ አገባብና አወጣጥን እውቀት የእከሌን መሞት ወይም ህያው መሆን ወይም መታመሙና የመሳሰሉትን ለወደፊት የሚከሰቱ ምድራዊ ክስተቶች ላይ ማስረጃ ለማድረግ የተማረ ሰው በርግጥም ከፊል ጥንቆላን ቀስሟል። ይህንኑ እውቀት ባበዛ ቁጥር ጥንቆላንም በርግጥ አብዝቷል በማለት ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።

فوائد الحديث

ኮኮብ ቆጠራ ክልክል መሆኑን እንረዳለን። እርሱም የኮኮቦችን ሁኔታ በመመርኮዝ የወደፊትን መናገር ነው። ምክንያቱም ይህ ተግባር የሩቅ እውቀትን ከመሞገት ውስጥ የሚመደብ ነውና።

ክልክል የሆነው ኮኮብ ማየት ተውሒድን የሚፃረር የሆነው የጥንቆላ አይነቱ ነው። አቅጣጫዎችን ወይም ቂብላን ለማወቅ ወይም ጊዜያቶችና ወራቶች መግባታቸውን ለማወቅ ኮኮቦችን ማየት ግን ፍቁድ ነው።

የኮኮብ እውቀትን መማር በጨመረ ቁጥር የጥንቆላ እውቀት ድርሻውም አብሮ ይጨምራል።

ኮኮቦች ሶስት ጥቅሞች ይሰጣሉ። እነሱም አላህ በተከበረ መጽሐፉ ውስጥ የጠቀሳቸው ናቸው፦ ሰማይን ማጌጥ ፣ አቅጣጫ የሚመራበት ምልክትና ሰይጣኖችን መውገሪያ ነው።

التصنيفات

ኢስላምን የሚያፈርሱ ነገሮች