'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'

'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'

ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦ 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላትን ከመተው አስጠነቀቁ። በሰውዬውና ሺርክና ክህደት ላይ በመውደቅ መካከል ያለው ግርዶ ሶላትን መተው እንደሆነም ተናገሩ። ሶላት ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛው ማእዘን ነው፣ በኢስላም ትልቅ ጉዳይ ነው። ግዴታነቱን አስተባብሎ የተወ ሰው በሁሉም ዑለማእ (የኢስላም ሊቃውንት) ስምምነት መሰረት ክዷል። በስንፍናና ድክመት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተወም እንደዚሁ ከሀዲ ነው። በዚህ ዙሪያ የሶሐቦች ሙሉ ስምምነት እንዳለም ተሰምቷል። አንዳንዴ የሚተው አንዳንዴ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ከባድ ዛቻ የተጋረጠ ይሆናል።

فوائد الحديث

ሶላትና በርሱ ላይ መጠባበቅ ያለውን አንገብጋቢነት እንረዳለን። ሶላት በክህደትና ኢማን መካከል ያለ መለያ ነው።

ሶላትን የተወና ያጓደሉ ሰው ላይ ብርቱ ማስጠንቀቂያ መምጣቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ኢስላምን የሚያፈርሱ ነገሮች, ክህደት (ኩፍር), የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ