'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው።

'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል: 'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው። ሓያእ (አይነ አፋርነትም) የኢማን አንዱ ክፍል ነው።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢማን ተግባሮችን፣ እምነቶችንና ንግግሮችን የጠቀለለ ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ተናገሩ። ከኢማን ክፍሎች ውስጥ በላጩና ከፍተኛው ትርጉሙን አውቆ ፣ የሚያስፈርደው በመተግበር "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው። አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑንና ለአምልኮ የተገባ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከርሱ ውጪ ያለ ማንም እንደማይገባውም ማመን ነው። የኢማን ትንሹ ስራ ሰዎችን የሚያውክ የሆነን ነገር ሁሉ ከመንገዳቸው ላይ ማስወገድ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሓያእ (አይነ አፋርነት) የኢማን አንድ ክፍል መሆኑን ተናገሩ። ይህም መልካም ለመስራትና ፀያፍ ለመተው የሚያነሳሳ ባህሪ ነው።

فوائد الحديث

ኢማን ከፊሉ ከከፊሉ የሚበላለጡ ደረጃዎች አሉት።

ኢማን ንግግርም፣ ተግባርም እምነትም ነው።

አላህን ማፈር ሲባል: በከለከለህ ስፍራ አለማየቱና ባዘዘክ ስፍራ አለማጣቱን ያስፈርዳል።

ቁጥር መወሳቱ በርሱ ላይ ብቻ መገደቡን አያሲዝም። ይልቁንም የኢማን ተግባራት እንዲሁ መብዛታቸውን ይጠቁማል። ዓረቦች ከዛ ቁጥር በላይ ያለን ውድቅ ማድረግ ሳይፈልጉም አንዳንድ ነገሮችን በቁጥር ገድበው ያወሱታል።

التصنيفات

የኢማን መጨመርና መቀነስ