إعدادات العرض
1- 'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው።
2- ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።
3- የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል።
4- ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው፤ ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
5- አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።
6- ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።