ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።

ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።

ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ልክ ያረጀ ልብስ እንደሚደክመው ሁሉ ኢማንም በአንዳችሁ ልብ ውስጥ ይደክማል። አላህ ኢማንን በልባችሁ ውስጥ እንዲያድስ ለምኑት።"

[ሶሒሕ ነው።] [Al-Haakim]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አዲስ ልብስን ለረጅም ጊዜ በመገልገላችን ምክንያት እንደሚደክም ሁሉ ኢማንም በሙስሊም ቀልብ ውስጥ እንደሚደክምና እንደሚያረጅ ተናገሩ። ይህም አምልኮ መፈፀምን በማቋረጥ ወይም ወንጀልን በመፈፀምና በስሜት ውስጥ በመዘፈቅ ምክንያት ነው። ስለዚህ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ግዴታ ነገሮችን በመፈፀም፣ ውዳሴና ምህረት መለመንን በማብዛት አላህ ኢማናችንን እንዲያድስልን እንድንለምነው ጠቆሙን።

فوائد الحديث

ፅናት እንዲሰጠንና በቀልባችን ውስጥ ኢማንን እንዲያድስልን አላህን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱ ፤

ኢማን ንግግርም ተግባርም እምነትም ሲሆን በአምልኮ (የአላህን ትዕዛዛት በመፈፀም) ሲጨምር በወንጀል ደግሞ ይቀንሳል።

التصنيفات

የኢማን መጨመርና መቀነስ