ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል…

ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።

አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- "ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በቻልነው መጠን መጥፎ ነገርን እንድንለውጥ ( እንድናስወግድ) አዘዋል። መጥፎ ነገር የሚባለውም፥ አላህና መልክተኛው የከለከሏቸው ሁሉም ነገሮች ናቸው። መጥፎ ነገርን ከተመለከተ አቅም ካለው በእጁ የመለወጥ 0(የማስወግድ)ግዴታ አለበት። ይህን ማድረግ ከተሳነው ደግሞ መጥፎ ነገር ፈፃሚውን በመከልከል፣ ጉዳቱን ለሱ በማብራራት፣ ከዚህ እኩይ ተግባር ፈንታ እሱን ወደ መልካም በመምራት በአንደበቱ ይለውጠው። ይህኛዉ የመለወጥ እርከን ከተሳነውም ይህን መጥፎ ነገር በመጥላት፣ ለመለወጥ አቅም ቢኖረው ኖሮ እንደሚለውጠው በመቁረጥ በቀልቡ ይለውጠው። በቀልብ መለወጥ (መጥላት) መጥፎ ነገርን የመለወጥ እጅግ ደካማው የኢማን እርከን ነው።

فوائد الحديث

ይህ ሐዲሥ መጥፎ ነገርን የማስወገድ እርከኖችን በማብራራት ረገድ መሰረት ነው ።

መጥፎን ነገር ደረጃ በደረጃ መከልከል እንደሚገባና፤ ሁሉም በችሎታውና በአቅሙ ልክ መከልከል እንደሚገባው መታዘዙ።

መጥፎን ነገር መከልከል ከማንም ላይ የማይወርድ ሀላፊነትና ሁሉም ሙስሊም በችሎታው ልክ እንዲሰራው የሚገደድበት የእስልምና ትልቅ ህግ (የዲን ምዕራፍ) ነው።

በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ከኢማን ክፍሎች መካከል አንዱ መሆኑ፤ እንዲሁም ኢማን የሚጨምርና የሚቀንስ መሆኑ።

ከመጥፎ ለመከልከል የሚከለክሉት ድርጊት መጥፎ መሆኑን ማወቅ መስፈርት ነው።

መጥፎን ነገር ለመለወጥ ከተቀመጡ መስፈርቶች መካከል ፦ ከሚለውጠው መጥፎ ነገር የባሰ መጥፎ ውጤት አለማስከተሉ አንዱ ነው።

እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ ከመጥፎ ለመከልከል የተቀመጡ ስርአቶችና መስፈርቶች አሉ።

መጥፎን ማውገዝ ሸሪዓዊ ብልሀት ፣ ዕውቀት እና እርግጠኝነት (ማስረጃ) ይፈልጋል።

በቀልብ አለማውገዝ የኢማን ድክመትን ይጠቁማል።

التصنيفات

የኢማን መጨመርና መቀነስ, በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ፍርድ, Principles of Enjoining Good and Forbidding Evil