إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡-…
የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል።
ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Kurdî English Kiswahili Español اردو Português বাংলা Bahasa Indonesia فارسی தமிழ் हिन्दी සිංහල Tiếng Việt മലയാളം Русский မြန်မာ ไทย پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Türkçe Bosanski Hausa తెలుగు دری Ελληνικά Azərbaycan Български Fulfulde ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek नेपाली Moore Oromoo Wolof Tagalog Soomaali Français Українська bm Deutsch ქართული Македонски Magyar 中文 rn km Malagasyالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት አብራሩ። እስልምናውን አሳምሮ፣ እውነተኛና ሙኽሊስ (ያጠራ) ሆኖ የሰለመ ሰው ከመስለሙ በፊት በሠራው ወንጀል አይጠየቅም። ወደ እስልምና ከገባ በኋላ ሙናፊቅ በመሆን ወይም ከእምነቱ በመውጣት መጥፎ የሠራ ግን በክህደት ዘመኑም ሆነ በእስልምና ዘመኑ ስለ ሠራው ሥራ ይጠየቃል።فوائد الحديث
ሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በጃሂሊያ ዘመን ለሰሩት ስራ የሰጡት ትኩረትና ፍርሃታቸውን እንረዳለን።
በእስልምና ላይ መፅናት መበረታታቱን እንረዳለን።
ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት እንረዳለን። እሱም ያለፈውን መጥፎ ስራዎች ማስማሩ ነው።
ከእስልምና የወጣና ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቀደም ብሎ ከመስለሙ በፊት ስለ ሠራቸው ሁሉ ሥራዎችና በእስልምና ውስጥም ስለ ሰራቸው ሁሉ ወንጀሎች ይጠየቃል።