إعدادات العرض
አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት።
አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት።
ከዓብደላህ ቢን መስዑድ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አላህ ከኔ በፊት በነበሩት ህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ለርሱ ከህዝቦቹ መካከል ሱናውን (ፈለጉን) የሚይዙና በትእዛዙ የሚመሩ ሐዋርያትና ባልደረቦች አሉት። ከነርሱ በኋላ ግን የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ምትኮች ይተካሉ። በእጁ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። በምላሱ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። በቀልቡ የታገላቸውም እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ ግን የጎመንዘር ዘለላ ያህል እንኳ ኢማን የለም።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া Oromoo پښتو ગુજરાતી ไทย മലയാളം Română नेपाली Malagasy Deutsch Fulfulde Кыргызча తెలుగు ქართულიالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው በፊት አላህ በህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ከህዝቦቹ መካከል የተመረጡ፣ ረዳቶች፣ ታጋዮች፣ ታማኞች፣ ከርሱ በኋላ ለተተኪነት የሚበጁ፣ ፈለጉን የሚይዙና ትእዛዙንም የሚከተሉ ባልደረቦች ይኖሩታል፤ ከዚያም ከነዚህ መልካም አበዎች በኋላ ግን ምንም መልካም የሌላቸው የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ሰዎች ይመጣሉ። በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። በምላሱ የታገላቸው እርሱም አማኝ ነው። በቀልቡም የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ ሰው ግን የጎመንዘር ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን እንደሌለው ተናገሩ።فوائد الحديث
በንግግራቸውም ይሁን በተግባራቸው ሸሪዓን የተፃረሩ ሰዎችን በመታገል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ውግዝን ነገር በቀልብ አለማውገዝ የኢማን መድከምን ብሎም መወገዱን ይጠቁማል።
አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ለነቢያቶች ከነርሱ በኋላ ተልእኳቸውን የሚሸከም ሰው እንዳገራ እንረዳለን።
መዳንን የፈለገ ሰው የነቢያቶችን ጎዳና መከተል ነው የሚገባው። ከነቢያቶች ጎዳና ውጪ ያለ ሁሉም መንገድ ጥፋትና ጥመት ነውና።
ጊዜው ከነቢዩ ‐ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ‐ እና ከሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘመን በራቀ ቁጥር ሰዎች ሱናዎችን ይተዋሉ፣ ዝንባሌያቸውን ይከተላሉ፣ አዳዲስ ቢድዓችም ይፈበረካሉ።
የጂሃድ ደረጃዎች መገለፃቸውን እንረዳለን። ጂሃድ በእጁ መለወጥ ለቻለ ሰው በእጅ ነው። መሪዎች፣ ሹማምንቶችና ሚኒስትሮችን ይመስል። ጂሃድ በንግግር ደግሞ እውነትን በማብራራትና ወደርሱ በመጣራት ይሆናል። ጂሃድ በቀልብ ደግሞ ውግዙን በቀልብ በማውገዝ፤ ባለመውደድ ወይም በርሱ ባለመደሰት ይሆናል።
በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።