አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ።…

አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባልደረቦች ወደነቢዩ በመምጣት እንዲህ ብለው ጠየቋቸው፦ " አንዳችን ለመናገር እጅግ የሚከብደንን ነገር ነፍሳችን ውስጥ እናገኘዋለን (በውስጣችን ይሰማናል)" እሳቸውም፦ "ይህን (በነፍሳችሁ ውስጥ) አገኛችሁን?" አሏቸው። እነሱም፦ "አዎን" አሉ። "ይህ ግልፅ ኢማን ነው።" በማለት መለሱላቸው።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

የተወሰኑ የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ባለደረቦች ወደርሳቸው በመምጣት አስቀያሚና እጅግ የሚፀየፉት በመሆኑ ሳቢያ ለመናገር የሚከብዳቸው የሆነ ነገር በነፍሳቸው ውስጥ ስለሚከሰት ትልቅ ጉዳይ ጠየቋቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ "ይህ በውስጣችሁ የተሰማችሁ ነገር ግልፅ ኢማንና ሰይጣን በልባችሁ የሚጥለውን ለመከላከል የሚያነሳሳችሁ እንዲሁም በነፍሶቻችሁ ውስጥ እሱን መናገር እንድታወግዙና እንዲከብዳችሁ የሚያደርግ የእምነት እርግጠኝነት ነው። ሰይጣን ልቦችችሁን አልተቆጣጠረምና ነው። ሰይጣን ልቡን የተቆጣጠረው ግን ውስጡ የሚሰማውን እንዳይናገረው የሚከለክለውን አያገኝም።" በማለት መለሱላቸው።

فوائد الحديث

ሰይጣን የኢማን ባለቤቶችን ከመወስወስ የዘለለ ምንም ነገር ማድረግ አለመቻሉ ደካማነቱን ይገልፅልናል።

ነፍስን የሚያማልሉ ጉትጎታዎችን አለማመንና አለመቀበል እንደሚገባ። ምክንያቱም ከሰይጣን ነው።

የሰይጣን ጉትጎታ አማኝን እንደማይጎዳ፤ ነገር ግን ከጉትጎታው በአላህ መጠበቅና በጉትጎታው ላይ ከማሰላሰል መቆጠብ እንደሚገባ።

አንድ ሙስሊም በእምነቱ ጉዳይ ግራ ያጋባውን ዝም ማለት እንደማይገባና ስለርሱ መጠየቅ እንደሚገባው ተረድተናል።

التصنيفات

በአላህ ማመን, የኢማን መጨመርና መቀነስ