ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።

ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ለተቸገረ (ባለዕዳ) ጊዜ የሰጠ ወይም ይቅር ያለ አላህ ከጥላው በስተቀር ጥላ በሌለበት የትንሳኤ ቀን ከዐርሹ ጥላ ስር ያስጠልለዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለተበዳሪ የእዳ መክፈያ ጊዜውን ያዘገየለት ወይም ያለበትን እዳ ከሱ ላይ ይቅር ያለ ምንዳው፦ የትንሳኤ ቀን ፀሀይ ወደ ሰዎች አናት ቀርባ ሀሩሯ በነሱ ላይ በሚበረታበት ወቅት አላህ ከዐርሹ ስር እንደሚያስጠልላቸው ተናገሩ። በዛን ቀንም አላህ ያስጠለለው ሰው ካልሆነ በስተቀር አንድም ሰው ጥላ አያገኝም።

فوائد الحديث

ለአላህ ባሮች ነገሮችን የማቅለል ትሩፋቱ፤ እሱም ከትንሳኤ ቀን መከራዎች የመዳኛ ምክንያት ነው።

ምንዳ የሚሰጠን በስራችን ልክ ነው።

التصنيفات

የመጨረሻው ህይወት