'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።

'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።' ዑመርም 'በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲከለክሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ራሴ በመናገርም ይሁን የሌላ ሰውን መሀላ ሳስተላልፍ በከለከሉት ምዬ አላውቅም።' አሉ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአባት መማልን እንደሚከለክል ተናገሩ። ስለዚህም መማል የፈለገ ሰው በአላህ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማል። ቀጥለውም ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲከለክሉ ከሰሙ ጀምሮ ሆን ብለውም ይሁን ሌላ ሰው ከአላህ ውጪ መማሉን በመናገር መልኩም ይሁን ምለው እንደማያውቁ አወሱ።

فوائد الحديث

ከአላህ ውጪ በሆነ አካል መማል ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ሐዲሡ ላይ በአባት መማል ብቻ የመጣው የጃሂሊያዎች (የድንቁርና ዘመን ሰዎች) ልማድ ስለነበር ነው።

ትክክለኛው መሀላ: አንድን ጉዳይ አፅንኦት ለመስጠት በአላህ ወይም በአላህ ስሞች ወይም በአላህ ባህሪያት መማል ነው።

የዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል፤ ይህም የታዘዙትን በፍጥነት በመተግበራቸው፣ በጥሩ አረዳዳቸውና በጥንቁቅነታቸው ነው።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል