ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።

ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።

ከአቡ አዩብ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሲገናኙ ይህም እየዞረ ያኛውም እየዞረ ወንድሙን ከሶስት ሌሊቶች በላይ ሊያኮርፈው አይፈቀድለትም። ከሁለቱ ምርጡ በሰላምታ የሚጀምረው ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙን አንዱ ሌላኛውን በሚያገኘው ጊዜ ሰላምታም ሳይሰጠውና ሳያናግረው ከሶስት ሌሊቶች በላይ ማኩረፍን ከለከሉ። ከነዚህ ሁለት ጠበኞች መካከል በላጩ ኩርፊያውን ለማስወገድ የሚሞክርና ሰላምታ የሚጀምረው ነው። እዚህ ሐዲስ ውስጥ ኩርፊያ በማለት የተፈለገው በነፍሱ ፍላጎቶች ያኮረፈ እንደሁ ነው። ወንጀለኞችን፣ የቢድዓ ባለቤቶችንና መጥፎ ጓደኞችን የመሰሉ ሰዎችን ለአላህ ሀቅ ብሎ ማኩረፍ ከሆነ ግን በወቅት ሳይሆን የሚገደበው ኩርፊያው በሚያመጣው ጥቅምና ያለባቸው ችግር በመወገዱ ላይ ነው የሚገደበው።

فوائد الحديث

የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ለመጠበቅ ሲባል ለሶስት ቀንና ከዛ በታች ማኩረፍ እንደተፈቀደ እንረዳለን። ለሶስት ቀናት ማኩረፉም ይቅር የተባለው ይህንኑ ተፈጥሯዊ ባህሪ ለማስተናገድ ሲባል ነው።

ሰላምታ ነፍሶች ውስጥ ያለን አለመግባባት ማስወገዱና የመዋደድ ምልክትም በመሆኑ የሰላምታን ደረጃ ያስረዳናል ፤

ኢስላም በወንድማማችነት ላይና በአማኞቹ አንድነት ዙሪያ መጓጓቱን እንረዳለን።

التصنيفات

ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት, ማኩረፍና መስፈርቶቹ, የሰላምታና የማስፈቀድ ስነ-ስርዓት