ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።

ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።"

[ሐሰን ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል። - አቡዳውድ ዘግበውታል። - አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሰው ልጅ ፍፁም ጓደኛውንና ባልደረባውን በልማዱና ኑሮው እንደሚመሳሰል፤ ጓደኝነትም በስነምግባር፣ በባህሪና የኑሮ ዘይቤ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ገለፁ። ለዚህም ጓደኛ አመራረጣችንን እንድናሳምር ጠቆሙ። ምክንያቱም ጥሩ ጓደኛ ወደ ኢማን፣ ቅናቻና መልካም ነገር ይጠቁማል። ለባልደረባውም አጋዥ ይሆናልና።

فوائد الحديث

መልካሞችን በመወዳጀትና በመምረጥ መታዘዙን፤ መጥፎዎችን መወዳጀት ደግሞ መከልከሉን እንረዳለን።

ከዘመድ ይልቅ ጓደኛን ብቻ ለይተው መጥቀሳቸው ጓደኛ አንተ ራስህ ነህ የምትመርጠው ስለሆነ፤ ወንድምና ቅርብ ዘመድ ግን አንተ ምንም ምርጫ ስለሌለህ ነው።

ጓደኛን መያዝ የግድ ከማስተዋል በኋላ የመጣ መሆን አለበት።

አንድ ሰው አማኞችን በመወዳጀት ዲኑን እንደሚያጠነክርና አመፀኞችን በመወዳጀት ደግሞ እንደሚያደክመው እንረዳለን።

التصنيفات

የመወዳጀትና የመራራቅ ህግጋት