إعدادات العرض
ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል።
ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል።
ከጃቢር ቢን ዓብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል። የወር መንገድ ሲቀር (ጠላቶች ውስጥ) ፍርሃት በመክተት ተረድቻለሁ፤ ምድር ለኔ መስገጃም ንፅህና መጠበቂያም ተደርጋልኛለች። ስለዚህ ከኡመቴ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰችበት ይስገድ። ምርኮ ለኔ ተፈቅዷል፤ ከኔ በፊት ለአንድም አካል አልተፈቀደችም። ምልጃ ተሰጥቶኛል። ነቢይ የሚላከው ወደ ህዝቦቹ ብቻ ነበር። እኔ ግን ወደ ሰው ባጠቃላይ ተልኬያለሁ።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Kiswahili සිංහල Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া Oromoo پښتو ગુજરાતી ไทย മലയാളം Română नेपाली Malagasy Deutschالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው በፊት ለነበረ ለአንድም ነቢይ ያልተሰጡ አምስት ነገሮች አላህ ለርሳቸው እንደሰጠ ተናገሩ: የመጀመሪያው: በፍርሃት ተረድቼያለሁ። በኔና በነርሱ መካከል የወር መንገድ ቢቀር ራሱ የጠላቶቼን ልብ ፍርሃት ይወራቸዋል። ሁለተኛው: ምድር ለኛ መስጂድ ተደርጋለች። የትም ብንሆን እንሰግዳለን። ውሃ መጠቀም በተሳነን ጊዜ ደሞ አፈሯ መፅጃ ተደርጎልናል። ሶስተኛ: ለኛ የጦርነት ምርኮ ተፈቅዶልናል። ይህም ሙስሊሞች ከከሃዲዎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚማርኩት ንብረት ነው። አራተኛ: ሰዎችን ከትንሳኤ ቀን መቆም ጭንቀት የምገላግልበት ትልቁ ምልጃ ተሰጥቶኛል። አምስተኛ: ወደ ፍጡራን ባጠቃላይ ወደ ሰዉም ወደ ጂኑም ሁሉ ተልኬያለሁ። ይህም ከርሳቸው በፊት ከነበሩት ነቢያት ተቃራኒ መሆኑ ነው። እነርሱ ይላኩ የነበሩት ወደ ህዝባቸው ብቻ ነበርና።فوائد الحديث
አንድ ሰው አላህን ለማመስገንና የተዋለለትን ፀጋ ይፋ ለማድረግ ብሎ የአላህን ፀጋዎች መቁጠሩ እንደተደነገገለት እንረዳለን።
አላህ ዐዘ ወጀል በነዚህ ጉዳዮች በኩል በዚህ ኡመት ላይና በነቢያቸው ላይ የዋለውን ችሮታ እንረዳለን።
በማንኛውም ሁኔታ ላይ ቢሆንም የሚችለውን ያህል መስፈርቶች፣ ማእዘናቶችና ግዴታዎችንም አሟልቶ ሶላትን በወቅቱ መስገድ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከነቢያቶች መካከል የተለዩበት ምልጃ የተለያዩ አይነት ምልጃዎች ናቸው: የመጀመሪያው: ለፍጡራን በመካከላቸው ፍርድ እንዲፈፀም የሚያማልዱ መሆናቸው፤ ሌላው: የጀነት ሰዎች ጀነት እንዲገቡ የሚያማልዱ መሆናቸው፤ ሌላው: ለአጎታቸው አቡ ጧሊብ ብቻ ከሀዲ ሆኖ ነውና የሞተው ከእሳት እንዲወጣ ሳይሆን እሳቱ እንዲቀልለት ማማለዳቸው ነው።
እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ያልተጠቀሱ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ብቻ የተሰጡ ነገሮች በርካታ ናቸው። ከነርሱም መካከል: ጠቅላይ የሆኑ ንግግሮች ተሰጥቷቸዋል፤ የነቢያት መደምደሚያ መሆናቸው፤ የኛ ሰልፍ እንደ መላዕክት ሰልፍ መደረጉና ሌሎችም ነገሮች ተለይቶ ተሰጥቷቸዋል።