የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።

የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።

የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ከሆኑት መካከል ከአንዷ እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደና ስለአንዳች ነገር የጠየቀው የአርባ ሌሊት ሶላቱ ተቀባይነት አይኖራትም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር ከመሄድ አስጠነቀቁ። (ይህም ጠንቋይን፣ ኮኮብ እየተመለከቱ የሚተነብዩን፣ ጠጠርን ተንተርሰው የሚተነብዩንና የመሳሰሉትን የሩቅ እውቀትን ለመሞገት ለመነሻ ያህል የሚጠቀሙን የሚያጠቃልል የወል ስም ነው።) የሩቅን እውቀት አዋቂ ነኝ ባይ ጋር በመሄድ ሩቅ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል አንዳችን መጠየቁ ብቻ በሱ ሳቢያ የአርባ ቀን የሶላቱን ምንዳ አላህ ይከለክለዋል። ይህም በዚህ ትልቅ ወንጀሉና ሀጢዐቱ ምክንያት መቀጣጫ እንዲሆነው ነው።

فوائد الحديث

የጥንቆላ ክልክልነትንና ወደጠንቋዮች በመሄድ ስለሩቅ ሚስጥር መጠየቅ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

ሰው ለወንጀሉ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ የመልካም ስራውን ምንዳ ሊከለከል እንደሚችል እንረዳለን።

አስትሮኖሚ (ዞዲያክ/ኮከብ ቆጠራ) በመባል የሚጠራው እውቀትና ወደርሱ መመልከት ፣ መዳፍና ሲኒን ለማወቅ ያህል ብቻ እንኳ ቢሆን ማንበብ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ይካተታል። ምክንያቱም ይህ ሁሉ ከጥንቆላና የሩቅ ምስጢር እውቀትን በመሞገት ውስጥ የሚመደብ ነውና።

ሩቅ ሚስጥር አዋቂ ነኝ ባይ ጋር የሄደ ሰው ምንዳው ይህ ከሆነ ራሱ ሩቅ ሚስጥር አዋቂ ነኝ ባዩ ምንዳው ምን ይሆን?

የአርባ ቀን ሶላቱ ስለምታብቃቃው ቀዳ የማውጣት ግዴታ አይኖርበትም። ነገር ግን በርሷ ምንም ምንዳ አያገኝም።

التصنيفات

ስሞችና ህግጋት