እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና

እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና

ከጃቢር አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው፦ አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ (ከተቀበልኩ) ከቆጠርኩና በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን “አዎን!” አሉት። እሱም፦ "በዚህ ላይ አንድንም ላልጨምር በአላህ እምላለሁ! " አለ።

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ሱና ፆሞችን ያልፆመ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።

فوائد الحديث

አንድ ሙስሊም መጨረሻው ጀነት መግባት እንዲሆን፥ ግዴታዎችን በመተግበር እና ክልከላን በመተው ላይ ጉጉት ሊኖረው ይገባል ።

ሐላል ፍቁድ ነገሮችን ፍቁድነታቸውን በማመን መተግበርና ክልክል ነገሮችን ክልክልነታቸውን በማመን መራቅ አሳሳቢ (ወሳኝ) ጉዳይ መሆኑን ፤

ግዴታዎችን መፈፀምና ክልክሎችን መተው ጀነት መግቢያ (ሰበብ) ምክንያት ነው።

التصنيفات

ስሞችና ህግጋት, የኢማን ቅርንጫፍ, የሶላት ትሩፋት