'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። ከኛ መካከል አንድም የለም በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት ቢሆን እንጂ። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ…

'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። ከኛ መካከል አንድም የለም በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት ቢሆን እንጂ። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። ከኛ መካከል አንድም የለም በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት ቢሆን እንጂ። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከገድ እምነት አስጠነቀቁ። እርሱም: በሚሰማም ይሁን በሚታይ ነገር፤ በበራሪም ሆነ በእንስሳም ሆነ በህመምተኞች (አካል ጉዳተኞች)፤ በቁጥሮችም ሆነ በቀናት ወይም ከነዚህ ውጪ ባሉ ማንኛውም ነገርም ቢሆን ገደ ቢስነትን ማመን ነው። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በራሪን የጠቀሱት ጃሂሊዮች ዘንድ የታወቀ ስለሆነ ነው። የዚህ ስራ መሰረቱም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ስራዎችን ለመጀመር ሲሉ በራሪን ይለቁና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ገድ አለኝ ብሎ ወደ ፈለገበት ጉዳይ ይሄዳል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ደግሞ ገደ ቢስ ነኝ ብሎ ያሰበውን ጉዳይ ከመፈፀም ይቆጠባል። ይህ ነገር ሺርክ መሆኑንም ተናገሩ። ገደቢስነትን ማመን ሺርክ የሆነውም መልካምን ከአላህ በቀር የሚያመጣ ስለሌለና፤ መጥፎንም ብቸኛና አጋር ከሌለው ከአላህ በቀር የሚከላከል ስለሌለ ነው። ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሙስሊም ቀልብ ውስጥ አንዳች ገደቢስ እምነት ሊከሰት እንደሚችል፤ ነገር ግን ሰበቡን ከማድረስ ጋር በአላህ ላይ በመመካት ማስወገድ እንዳለበት ገለፁ።

فوائد الحديث

የገድ እምነት ልብን ከአላህ ውጪ በሆነ አካል ማንጠልጠል ስላለበት ሺርክ ነው።

አንገብጋቢ ጉዳዮች ልብ ውስጥ እንዲፀኑና እንዲሸመደዱ መደጋገሙ ወሳኝ እንደሆነ እንረዳለን።

የገድ እምነትን በአላህ ላይ መመካት ያስወግደዋል።

ብቸኛ በሆነው በአላህ ላይ መመካት መታዘዙንና ልብም በርሱ ላይ መንጠልጠል እንዳለበት እንረዳለን።

التصنيفات

ማጋራት (ሺርክ), የቀልብ ተግባራት ትሩፋቶች