ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ።

ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ።

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ። ይህንን ከፈፀሙ በኢስላም ሐቅ ካልሆነ በቀር ደማቸውና ገንዘባቸውን ከኔ ጠብቀዋል። ሒሳባቸውም አላህ ዘንድ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አጋርያን ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ብቸኛና አጋር እንደሌለው እስኪመሰክሩ፤ በሙሐመድም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት እስኪመሰክሩና ይህ የምስክር ቃል በሚያስፈርደው ነገሮች እስከሚተገብሩ ለምሳሌ በቀንና ምሽት ውስጥ አምስት ሶላቶችን መስገድ ላይ መጠባበቅ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ ለሚገባው እስኪሰጡ ድረስ አላህ አጋርያንን እንዲጋደሉ እንዳዘዛቸው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ። እነዚህን ጉዳዮች የሰሩ ጊዜ ኢስላም ደማቸውንና ገንዘባቸውን ይጠብቅላቸዋል። በኢስላም ህግጋት መሰረት ለግድያ የሚያበቃቸውን ወንጀል ወይም ጉዳት እስካልፈፀሙ ድረስም እነርሱን መግደል አይፈቀድም። ከዚያም እነርሱን መተሳሰቡን የትንሳኤ ቀን ውስጣቸውን በሚያውቀው አላህ ቁጥጥር ይሆናል።

فوائد الحديث

ህግጋቶች ተፈፃሚነታቸው በውጫዊ ማንነት መሰረት ነው። ውስጣዊ ማንነትን የሚቆጣጠረው አሏህ ነው።

ወደ ተውሒድ የመጣራት አንገብጋቢነትን እንረዳለን። ዳዕዋ በቅድሚያ የሚጀመረው በተውሒድ ነው።

ይህ ሐዲሥ አጋርያንን ወደ ኢስላም እንዲገቡ ማስገደድ ይገባል ማለት አይደለም። ይልቁንም ወደ ኢስላም በመግባት ወይም ግብር በመክፈል መካከል የመምረጥ ምርጫ አላቸው። ወደ ኢስላም የሚደረግን ዳዕዋ በመከልከል ላይ የሙጥኝ ካሉ ግን በኢስላም ህግጋት መሰረት እነርሱን ከመጋደል ውጪ ሌላ ምንም አማራጭ አይኖርም።

التصنيفات

ኢስላም