ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።

ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።

ከበራእ ቢን ዓዚብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ቀብር ውስጥ በተጠየቀ ጊዜ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል።" ይህም አላህ እንዲህ እንዳለው ነው: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አማኝ ቀብር ውስጥ ይጠየቃል። ለዚህ ስራ የተወከሉ ሁለት መላእክት ይጠይቁታል። እነሱም በበርካታ ሐዲሦች ስማቸው እንደተጠቀሰው ነኪርና ሙንከር ናቸው። ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ይመሰክራል። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ነው አላህ የተረጋገጠው ቃል ብሎ የተናገረበት አሉ: {አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ህይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል።} [ኢብራሂም:27]

فوائد الحديث

የቀብር ጥያቄ እውነት እንደሆነ እንረዳለን።

አላህ በዱንያም ይሁን በመጪው ዓለም አማኝ ባሮቹን በተረጋገጠው ቃል ላይ በማርጋት ለነርሱ ያለውን ችሮታ እንረዳለን።

የተውሒድ ምስክርነት ትሩፋትንና በርሷ ላይ የመሞትን ደረጃ እንረዳለን።

አላህ አማኝን በዱንያ በኢማን ላይ በማርጋት፣ ቀጥተኛውን መንገድ በማስያዝ፤ ሲሞት ደግሞ በተውሒድ ላይ እንዲሞት በማድረግ፤ በቀብር ውስጥ ደግሞ ሁለቱ መልአኮች ሲጠይቁት ማፅናቱን እንረዳለን።

التصنيفات

የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት