የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።

የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።

ከአቡ ሲርመህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የጎዳ ሰው አላህም ይጎዳዋል ፤ ያስጨነቀንም አላህም ያስጨንቀዋል።"

[ሐሰን ነው።] [ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነፍሱም ይሁን በገንዘቡም ይሁን በቤተሰቡም ይሁን በማንኛውም ጉዳዩ ላይ ሙስሊም ላይ ጉዳትና ችግርን ከማድረግ አስጠነቀቁ። ይህንንም ለፈፀመ አላህም በሰራው አምሳያ እንደሚመነዳውና እንደሚቀጣው ገለፁ።

فوائد الحديث

ሙስሊምን መጉዳትና ማስጨነቅ መከልከሉን ፤

አላህ ለባሮቹ የሚበቀል መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

የመወዳጀትና የመራራቅ ህግጋት