ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ አንሷሮች እንዲህ አሉ: "አማኝ እንጂ አይወዳቸውም፤ ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም። አንሷሮችን የወደደ አላህ ይወደዋል።…

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ አንሷሮች እንዲህ አሉ: "አማኝ እንጂ አይወዳቸውም፤ ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም። አንሷሮችን የወደደ አላህ ይወደዋል። አንሷሮችን የጠላ አላህ ይጠላዋል።

ከበራእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ አንሷሮች እንዲህ አሉ: "አማኝ እንጂ አይወዳቸውም፤ ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም። አንሷሮችን የወደደ አላህ ይወደዋል። አንሷሮችን የጠላ አላህ ይጠላዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመዲና ነዋሪ የሆኑትን አንሷሮች መውደድ የኢማን መሙላት ምልክት መሆኑን ተናገሩ። ይህም የሆነው ኢስላምንና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመርዳት ላይ፣ ሙስሊሞችን በማስጠጋት ላይ ባደረጉት ልፋት፣ ገንዘቦቻቸውንና ነፍሳቸውንም በመለገስ በኩል ቀዳሚ ስለሆኑ ነው። እነርሱን መጥላትም የንፍቅና ምልክት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንሷሮችን የወደደ አላህ እንደሚወደው እነሱን የጠላም አላህ እንደሚጠላው ገለፁ።

فوائد الحديث

እዚህ ሐዲሥ ውስጥ የአንሷሮች ትልቅ ደረጃ ተገልጿል። እነርሱን መውደድም የኢማንና ከንፍቅና የመጥራት ምልክት ነው።

የአላህን ወዳጆች መውደድና መርዳት አላህ ባሪያውን የሚወድበት አንዱ ምክንያት ነው።

በእስልምና ቀዳሚ የሆኑት የመጀመሪያቹ ያላቸውን ደረጃ እንረዳለን።

التصنيفات

የኢማን ቅርንጫፍ, የኢማን ቅርንጫፍ, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ, የሶሐቦች (ረዺየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ