‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›

‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: ‹ከሰዎች ሁሉ መጥፎዎቹ እነሱ በህይወት እያሉ ሰአቲቷ (ቂያማ) የምታገኛቸውና መቃብሮችን መስገጃ አድርገው የሚይዙት ናቸው።›"

[ሐሰን ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ መጥፎ ሰዎች ተናገሩ። እነርሱም በህይወት ሳሉ ሰአቲቱ (ቂያማ) የምትቆምባቸውና እነዚያ መቃብሮችን መስገጃ አድርገው በመያዝ እርሱ ዘንድና ወደርሱ በመዞር የሚሰግዱት ናቸው።

فوائد الحديث

ወደ ሺርክ ስለሚያዳርስ መቃብሮች ላይ መስገጃ መገንባት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

መስጂድ ማለት ባይገነባበት እንኳ የሚሰገድበትን ስፍራ የሚጠቁም ስያሜ ስለሆነ ባይገነባበት እንኳ መቃብር ዘንድ መስገድ ክልክል ነው።

የደጋጎችን መቃብር ለሶላት መስገጃነት የያዘ ሰው ወደ አላህ መቃረብን አስቦ እንደሆነ ቢሞግት እንኳ ከሰዎች ሁሉ መጥፎ ነው።

التصنيفات

የትንሳኤ ምልክቶች