إعدادات العرض
አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት
አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල ไทย دری Akan Azərbaycan Български Fulfulde Magyar ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių नेपाली or Română Kinyarwanda тоҷикӣ O‘zbek Moore Wolof Oromoo Soomaali bm Українська rn km Српски ქართული Македонски Ελληνικάالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቀብራቸውን በማላቅና የሱጁድ አቅጣጫውን ወደዛው በማድረግ ሰዎች ቀብራቸውን እንደሚያመልኩት ጣኦት እንዳያደርግባቸው አምላካቸውን ተማፀኑ፤ ከዚያም የነቢያቶችን መቃብር የአምልኮ ስፍራ አድርገው በሚይዙ ላይ የአሏህ እርግማን እንደሰፈነባቸውና ከእዝነቱም እንዳባረራቸው አሳወቁ። ምክንያቱም መቃብሩን የአምልኮ ስፍራ አድርጎ መያዝ የቀብሩን ባለቤት እንዲመለክ ለማድረግና በተቀበረበት አካል ዙርያ አጉል እምነት ለማሳደር መዳረሻ ነውና።فوائد الحديث
የነብያትና የጻድቃን ሰዎች መቃብርን በተመለከተ ሸሪዓው ያስቀመጠውን ገደብ ማለፉ ከአላህ ሌላ የሚመለኩ ጣኦት እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ወደ ሽርክ (ሽርክ) ከሚመሩ መንገዶች መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
ቀብሩ ውስጥ የተቀበረው አካል ወደ አሏህ ምንም አይነት ቅርበት ቢኖረውም ቀብሩን ለማላቅም ይሁን በመቃብሩ አሏህን ለማምለክ ማለም አይፈቀድም።
መስገጃን መቃብር ላይ መገንባት የተከለከለ ነው።
ሟቹ ላይ ሶላተል ጀናዛ ያልሰገደበት ሰው ቀብሩ ዘንድ መስገድ ይፈቀድለታል። ከዛ ውጪ ግን መስጂድ ባይገነቡ እንኳ መቃብር ዘንድ መስገድ የተከለከለ መሆኑን እንረዳለን።