إعدادات العرض
እንዳትገድለው! ከገደልከው እርሱ ከመግደልህ በፊት የነበርክበት ደረጃ ላይ ይሆንና አንተ ደሞ የተናገረውን ንግግር ከመናገሩ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ ትሆናለህ።" አሉ።
እንዳትገድለው! ከገደልከው እርሱ ከመግደልህ በፊት የነበርክበት ደረጃ ላይ ይሆንና አንተ ደሞ የተናገረውን ንግግር ከመናገሩ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ ትሆናለህ።" አሉ።
ከሚቅዳድ ቢን ዐምር አልኪንዲይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ለአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አላቸው: «ከከሀዲዎች መካከል ከአንዱ ጋር ብንገናኝና ብንጋደል አንድ እጄንም በሰይፉ መቶ ቢቆርጣት ከዚያም ከኔ ለማምለጥ ወደ ዛፍ ተጠግቶ ለአላህ ብዬ እስልምናን ተቀብያለሁ ቢል የአላህ መልክተኛ ሆይ! ንገሩኝ እስኪ ይህን ከተናገረ በኋላ ልግደለውን? የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው።" አሉ። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንድ እጄን‘ኮ ቆርጧል። ከዚያም እጄን ከቆረጣት በኋላ ነው ይህቺን የተናገራት!" አለ። የአላህ መልክተኛም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እንዳትገድለው! ከገደልከው እርሱ ከመግደልህ በፊት የነበርክበት ደረጃ ላይ ይሆንና አንተ ደሞ የተናገረውን ንግግር ከመናገሩ በፊት በነበረው ደረጃ ላይ ትሆናለህ።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Português සිංහල Nederlands অসমীয়া Tiếng Việt Kiswahili ગુજરાતી پښتو Oromoo ไทย Hausa Română മലയാളം नेपाली Deutsch Malagasy Кыргызчаالشرح
ሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና -ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጦርነት ላይ ከአንድ ከሀዲ ሰው ጋር ቢገናኝና በሰይፍ ብቻ ለብቻ ቢጋጠሙ ከሀዲውም አንድ እጁን በሰይፍ አግኝቶ ከቆረጠ በኃላ ከርሱ ሸሽቶ በዛፍ ቢመሸግና "ላኢላሃ ኢለሏህ" ቢል እጄን ከቆረጠ በኋላ እርሱን መግደል ይፈቀድልኛልን? በማለት ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳትገድለው! አሉት። እርሱም: የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሱ’ኮ አንድ እጄን ቆርጧል። ይህን ከማድረጉም ጋር አልገድለውምን? አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እንዳትገድለው! እርሱ ደሙን ማፍሰስ ከተከለከሉት ሆኗል። ከሰለመ በኋላ ከገደልከው እርሱ በእስልምናው ደሙ የተጠበቀ ስለሆነ ባንተ ደረጃ ይሆንና አንተ ደሞ እርሱን በመግደልህ በቂሷስ ህግ መሰረት ደምህ መፍሰሱ የተፈቀደ ስለምትሆን በርሱ ደረጃ ላይ ትሆናለህ! አሉት።فوائد الحديث
ወደ እስልምና መግባቱን የሚጠቁም ንግግር ወይም ተግባር የተስተዋለበትን ሰው መግደል ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
ከከሃዲዎች መካከል አንዱ በጦርነት መሀል ከሰለመ እስልምናን የሚቃረን ነገር በግልፅ እስካልታየበት ድረስ ደሙ የተጠበቀና እርሱን ከመጉዳት መቆጠብም ግዴታ ይሆናል።
አንድ ሙስሊም ዝንባሌው ለወገንተኝነትና ለበቀል ሳይሆን ሸሪዓን የተከተለ መሆኑ ግዴታ ነው።
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ይህ ታሪክ አልተከሰተም የሚለው ሚዛን ይደፋል በሚለው አቋም ላይ ተመስርተን ድንገታዊ ክስተቶች ከመከሰታቸውም በፊት (ያላቸውን ኢስላማዊ ፍርድ) መጠየቁ ይፈቀዳል የሚልን እንረዳለን። ከአንዳንድ ሰለፎች ሳይከሰት መጠየቅ እንደሚጠላ የተዘገበው መከሰቱ ያልተለመደ የሆኑ ጉዳዮችን በሚል ይተረጎማል። በተለምዶ ሊከሰቱ የሚመቹ ጉዳዮችን ለማወቅ መጠየቅ ግን የተደነገገ ነው።
التصنيفات
ኢስላም