ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር

ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት ከመግባት ራሱን ያቀበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ህዝባቸው ጀነት እንደሚገቡ ተናገሩ። ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ። እሳቸውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም : "መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከተለና የታዘዘ ጀነት ገባ። ያመፀና ለሸሪዐ ታዛዥ ያልሆነ ሰው ግን በርግጥም በመጥፎ ስራዎቹ ጀነት ከመግባት ራሱን አቅቧል።" በማለት መለሱላቸው።

فوائد الحديث

መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ አላህን ከመታዘዝ ይመደባል። እሳቸውን ማመፅም አላህን ከማመፅ ይመደባል።

ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ ጀነት መግባትን ስታስፈርድ እሳቸውን ማመፅ ደግሞ እሳት መግባትን የምታስፈርድ መሆኗ።

ከዚህ ኡማህ አላህና መልክተኛውን ያመፁ ሲቀሩ ነቢዩን ታዛዥ ለሆኑ ብስራት ነው፤ ሁሉም ጀነት ይገባሉና።

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ላይ ያላቸውን እዝነትና እንዲመሩ ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት እንረዳለን።

التصنيفات

ነቢያችን ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና