إعدادات العرض
ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።
ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው። ወደ ጥመት የተጣራ ሰውም የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ወንጀል ይኖርበታል። ይህም (በርሱ ላይ የሚኖረው ወንጀል) ከወንጀሎቻቸው ምንም ሳይቀነስ ነው።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Tiếng Việt नेपाली Malagasy Kinyarwanda తెలుగు Lietuvių Oromoo Română മലയാളം Nederlands Soomaali Српски Українська Deutsch ಕನ್ನಡ Wolof Moore Shqip ქართული Azərbaycan Magyarالشرح
በንግግሩ ወይም በተግባሩ እውነትና መልካም ወዳለበት መንገድ ሰዎችን የመራ፣ የጠቆመና የቀሰቀሰ ሰው የተከታዩን አምሳያ ምንዳ እንደሚያገኝና ይህም ከተከታዩ ምንዳ አንዳችም ሳይቀነስ እንደሆነ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ። በንግግር ወይም በተግባር ወንጀልና ኃጢአት ወይም የማይፈቀድ ነገር ወዳለበት የጥመትና የክፋት መንገድ ሰዎችን የጠቆመ ሰውም የተከታዩን አምሳያ ወንጀልና ኃጢአት ይኖርበታል። ይህም ከነርሱ ወንጀል አንዳችም ሳይቀነስ ነው።فوائد الحديث
በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ቅናቻ መጣራት ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ተጣሪ ሰው በርሱ ጥሪ የሰሩ ሰዎችን ምንዳ አምሳያ ይኖረዋል። ይህም የአላህን ትልቅ ችሮታና ሙሉ ቸርነት ያስረዳናል።
በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ጥመት የመጣራትን አደጋ እንረዳለን። ወደ ጥመት የሚጣራም ሰው በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
ምንዳ የሚሰጠው በስራው አይነት እንደሆነ እንረዳለን። ወደ መልካም የተጣራ ሰው በጥሪው የሰራን ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። ወደ መጥፎ የሰበከ ሰውም በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
አንድ ሙስሊም ወንጀልን ግልፅ በማድረጉ ሰዎች አይተው እንዳይከተሉት መጠንቀቅ አለበት። በዚህ ላይ ሆን ብሎ ባይቀሰቅስ እንኳ በተከተሉት ሰዎች ልክ ወንጀል ላይ ይወድቃልና።
التصنيفات
ቢድዓ