إعدادات العرض
ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል…
ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ"
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी বাংলা Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் සිංහල မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە ไทย دری Кыргызча or Kinyarwanda नेपाली Română Lietuvių Malagasy ಕನ್ನಡ Oromoo Nederlands Soomaali Српски Українська Wolof Moore ქართული Azərbaycan Magyar Tagalogالشرح
'ከዚህ ሕዝብ (ኡመት) ሆኖ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥሪ የደረሰውና ስለርሳቸው የሚሰማ ሆኖ ከዚያም በርሳቸው ሳያምን የሚሞት አንድም አይሁዳዊም ይሁን ክርስቲያን ወይም ሌላ እምነት ተከታይ የለም ዘልአለሙን የእሳት ሰው ቢሆን እንጂ።' ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማሉ።فوائد الحديث
የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልክተኝነት ዓለምን በሙሉ የሚጠቀልል መሆኑን፣ እሳቸውን መከተልም ግዴታ መሆኑን፣ በሳቸው ድንጋጌ ሁሉም ድንጋጌዎች መሻራቸውንም እንረዳለን።
በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የካደ ሰው ከሳቸው ውጪ ባሉ ነቢያቶች የአላህ ሶላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይስፈንና እንደሚያምን መሞገቱ አይጠቅመውም።
ስለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልሰማና የኢስላም ጥሪ ያልደረሰው ሰው ተቀባይነት ያለው ምክንያት ስላለው የርሱ ጉዳይ በመጨረሻው አለም አላህ ዘንድ ነው።
ነፍስ ልትወጣ ጉሮሮ ላይ እስካልደረሰች ድረስ ከባድ በሽታ ላይ ሆኖ እንኳ ቢሆን የሰለመ እስልምናው ከመሞቱ በፊት እስከሆነ ድረስ በኢስላም የሚገኘው ጥቅም የተረጋገጠ ነው።
የከሀዲያንን ሃይማኖት ትክክለኛ እምነት አድርጎ ማሰብ ክህደት ነው። (ከነርሱም ውስጥ አይሁድና ክርስትና ይገኛሉ።)
አይሁድና ክርስትናን በሐዲሡ ውስጥ መጠቀሳቸው ከነርሱ ውጪ ያሉትን አፅንኦት ለመስጠት ነው። ይህም አይሁድና ክርስቲያኖች መጽሐፍ እያላቸውም የነርሱ ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ከነርሱ ውጪ መጽሐፍ የሌላቸው ደሞ በበለጠ መልኩ መንገድ የሐዲሡ መልእክት ውስጥ ይገባሉ። ስለሆነም ሁሉም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እምነትና መመርያ ውስጥ መግባት ግዴታቸው ነው።