የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት…

የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።

ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደድ፣ ከማዘን፣ ከመርዳት፣ ከማገዝና እነርሱ ላይ በሚደርስ ጉዳት አብሮ ከመጎዳት አንፃር ሙስሊሞች ከፊሉ ለከፊሉ ሊኖረው የሚገባውን ሁኔታ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ምሳሌ ሊሆን እንደሚገባው ግዴታነቱን ገለፁ። አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው አካል በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት አብሮት ይሰቃያል።

فوائد الحديث

የሙስሊሞችን ሐቅ ማላቅ፤ እነርሱን በማገዝና ከፊሉ ለከፊሉ ማዘን ላይ ማነሳሳት ይገባል።

በእምነት ባለቤቶች መካከል መዋደድና መረዳዳት ሊኖር ይገባል።

التصنيفات

ኢስላም