አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል

አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዐስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል።" እንዲህም አሉ፦ " ዐርሹ ውኃ ላይ ነው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በፍጡራኖች ላይ የሚከሰተውን ውሳኔዎች ህይወት፣ ሞት፣ ሲሳይና ሌሎችንም ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት በዝርዝር በጥብቅ ሰሌዳ ውስጥ እንደፃፈውና እሱም አላህ በወሰነው መልኩ የሚከሰት መሆኑን ተናገሩ። ሁሉም የሚከሰቱ ነገሮች በአላህ ፍርድና ውሳኔ መሰረት ነው። አንድ ሰውን ያገኘው ነገር ቀድሞውኑ ሊስተው አይችልም ነበር፤ የሳተውም ነገር ሊያገኘው አይችልም ነበር።

فوائد الحديث

በአላህ ፍርድና ቅድመ ውሳኔ ማመን ግዴታ መሆኑን እንረዳለም።

ቀደር (ውሳኔ) ሲባል :- አላህ በነገሮች ላይ ያለውን ዕውቀት፣ መፃፉን፣ መሻቱንና መፍጠሩን የሚያጠቃልል ነው።

ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ውሳኔዎች እንደተፃፉ ማመን በሚያጋጥሙን ነገሮች መውደድና መቀበልን ይፈይደናል።

ሰማያትና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት የአርረሕማን ዐርሽ ውኃ ላይ ነበር።

التصنيفات

የቀዷና ቀደር ደረጃዎች