إعدادات العرض
በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው።
በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው።
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው። የትንሳኤ ቀን ሰዎች በስራዎቻቸው የተመነዱ ጊዜ ለነርሱ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ይላቸዋል፦ 'እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ?' "
[ሐሰን ነው።] [አሕመድ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá සිංහල தமிழ் ไทย دری Кыргызча or Kinyarwanda नेपाली Română Malagasy Lietuvių Oromoo Nederlands Soomaali Српски Українська ಕನ್ನಡ Wolof Moore ქართული Azərbaycan Magyar Македонскиالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ላይ እጅግ የሚፈሩት ነገር ትንሹን ሺርክ እንደሆነ እሱም ይዩልኝ እንደሆነ ተናገሩ። ይሀውም ለሰዎች ብሎ መስራቱ ነው። ቀጥለውም ለይዩልኝ የሚሰሩ ሰዎች የትንሳኤ ቀን የሚጠብቃቸውን ቅጣት ተናገሩ። ለነርሱ: "እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ? ለዚህ ስራችሁ ለናንተ መመንዳትና አጅር መስጠት ይችላሉን?" እንደሚባሉም ተናገሩ።فوائد الحديث
ስራን ለአላህ ማጥራት ግዴታነቱንና ከይዩልኝም መጠንቀቅ እንዳለብን እንረዳለን።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለኡመታቸው ያላቸውን ከባድ እዝነት፣ በመመራታቸው ላይ ያላቸውን ጉጉትና ለነርሱ ያላቸውን ተቆርቋሪነት እንረዳለን።
ሶሐቦች የደጋጎች አለቃ ከመሆናቸውም ጋር ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ሲያናግሩ በዚህ ልክ የሚፈሩላቸው ከሆነ ከነርሱ በኋላ ባሉ ሰዎች ላይ ያላቸው ፍርሀት እጅግ የከበደ መሆኑን እንረዳለን።