إعدادات العرض
አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ!
አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ!
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: አንድ እለት ከአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኋላ ሳለሁ እንዲህ አሉኝ "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁኝ! አላህን ጠብቅ ይጠብቅሀል፤ አላህን ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ ፅፎብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ጽሑፉም ደርቋል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili فارسی தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Malagasy тоҷикӣ Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan Tagalog ქართული bm Lingala Македонскиالشرح
ኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር እየጋለበ ሳለ ለሱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል : እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አሳውቅሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎች የአላህ ጥበቃና ወደየትም ብትዞር የቸገረህን በመርዳት አላህም የሚጠብቅህ ይሆናል። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! የጠያቂዎችን ልመና የሚቀበለው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አለህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማይደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም።فوائد الحديث
ህፃናትና ትናንሽ ልጆችን እንደ ተውሒድ፣ አዳቦችና ሌሎችንም የዲን ጉዳዮችን የማስተማር አንገብጋቢነት ፤
ምንዳ በስራው አይነት እንደሆነ ፤
ከሱ ውጪ ያለን ሁሉ በመተው በአላህ ላይ ብቻ መደገፍና በሱ ላይ ብቻ መመካት መታዘዙን ፤ እሱስ ምንኛ ያማረ መመኪያ ነው!
በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመንና በፍርዱ መውደድ እንዳለብን ፤ አላህ ሁሉንም ነገር ወስኗልና።
የአላህን መመርያ የጣሰ ሰው አላህ ያጠፋዋል እንጂ እንደማይጠብቀው ተምረናል።
التصنيفات
የቀዷና ቀደር ደረጃዎች