'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'

'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፡ "በካዕባ ይሁንብኝ በፍፁም!" ኢብኑ ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲሁ አሉ፡ "ከአሏህ ውጭ ባለ አካል አይማልም! ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁና 'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]

الشرح

በአሏህ ወይም በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር ከዛ ውጪ በሆነ መሀላ የማለ ሰው በአላህ ክዷል ወይም አጋርቷል እያሉን ነው። ምክንያቱም በአንድ አካል መማል እሱን ማላቃችንን ያስፈርዳል፤ በእውነቱ ልቅና ደግሞ የሚገባው ለአሏህ ብቻ ነው። ስለዚህም በሱ ወይም ከስምና ባህሪዎቹ መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር አይማልም። ይህ መሀላ ከትንሹ ሽርክ የሚመደብ ነው። ይሁን እንጂ የማለው ሰው የማለበትን አካል እንደ አሏህ ወይም ከዛም በላይ አልቆት ከሆነ ግን መሃላው ትልቁ ሽርክ ይሆናል።

فوائد الحديث

በመሀላ ማላቅ ጥራት የተገባው የአሏህ ሐቅ ነው። በመሆኑም በአላህ ፣ በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማልም።

ሰሓቦች በመልካም ለማዘዝ እና ከመጥፎ ለመከልከል የነበራቸውን ጉጉት ያሳያል፤ በተለይም ጥፋቱ ሽርክን ወይም ክህደትን የሚመለከት ሲሆን የበለጠ ጉጉት አላቸው።

التصنيفات

ማጋራት (ሺርክ)