'አንተ አለቃችን የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የሁሉም አለቃው አላህ ነው።' አሉ። እኛም 'በደረጃ በላጫችን እጅግ ታላቅ የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የምትሉትን በሉ ወይም ከምትሉት…

'አንተ አለቃችን የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የሁሉም አለቃው አላህ ነው።' አሉ። እኛም 'በደረጃ በላጫችን እጅግ ታላቅ የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የምትሉትን በሉ ወይም ከምትሉት ከፊሉን በሉ ሰይጣን (ወደ ወሰን ማለፍ እንዳይጎትታቹ) አይጫወትባችሁ' አሉ።

ከዐብደላህ ቢን ሺኺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «ከበኒ ዓሚር ልዑካን ጋር ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሄድኩ። 'አንተ አለቃችን የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የሁሉም አለቃው አላህ ነው።' አሉ። እኛም 'በደረጃ በላጫችን እጅግ ታላቅ የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የምትሉትን በሉ ወይም ከምትሉት ከፊሉን በሉ ሰይጣን (ወደ ወሰን ማለፍ እንዳይጎትታቹ) አይጫወትባችሁ' አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ልኡካኖች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ወደርሳቸውም የደረሱ ጊዜ እርሳቸውን ለማሞገስ ፈልገው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልወደዷቸውን የተወሰኑ ንግግሮች ተናገሩ። "አንቱ አለቃችን የሆኑ!" አሏቸው። ነቢዩም ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የሁሉም አለቃ አላህ ነው።" በፍጡራኑ ላይ የተሟላ አለቃነት የርሱ ነው። ፍጡራን ባሮቹ ናቸው። "በደረጃ በላጫችን የሆኑ" አሉ። ማለትም በደረጃ፣ በልቅና ከፍ ያሉ ማለት ነው። "እጅግ ታላቅ የሆኑ" በጣም ለጋስ፣ ከፍታና ልቅና ያለዎት ለማለት ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተለመደውን ንግግራቸውን እንዲናገሩ፣ በቃላቶች ወሰን እንዳያልፉና ክልክል ወደሆነው ሺርክና መዳረሻዎቹ ለሚዳርገው ወሰን ማለፍና ያልተገባ ሙገሳም ሰይጣን እንዳይጎትታቸው (መጠንቀቅ እንዳለባቸው) ሱሓቦችን ጠቆሙ።

فوائد الحديث

በሶሐቦች ነፍስ ውስጥ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ደረጃ የላቀ መሆኑንና ለርሳቸው ያላቸውን ክብር እንረዳለን።

በንግግር ወሰን ማለፍ መከልከሉንና በአነጋገር ሚዛናዊ መሆን እንደሚገባ እንረዳለን።

ተውሒድ ከሚያጎድፉት ንግግሮችም ሆነ ተግባራት ጥበቃ እንደተደረገለት እንረዳለን።

በማወደስ ወሰን ከማለፍ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ከሰይጣን መግቢያዎች አንዱ ነው።

በሐዲሱ የተጠቀሰው ንግግራቸው ለመተናነስ ያህልና ሰዎቹ በርሳቸው ላይ ወሰን እንዳያልፉ ስለፈሩ እንጂ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የአደም ዘር አለቃ ናቸው።

التصنيفات

ነቢያችን ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና