إعدادات العرض
በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी বাংলা ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල ไทย دری Кыргызча Lietuvių Kinyarwanda नेपाली Malagasy Italiano or ಕನ್ನಡ Oromoo Română Soomaali Српски Wolof Українська Moore Tagalog Azərbaycan ქართული Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለሙናፊቆችና ሶላት መገኘት ላይ በተለይ የዒሻእና ፈጅር ሶላት ላይ ስላላቸው ስንፍና፤ እነርሱ ሁለቱን ሶላት ከሙስሊም ጀመዓ ጋር መስገድ የሚያስገኘውን አጅር እና ምንዳ መጠን ቢያውቁ ኖሮ ህፃን ልጅ በሁለት እጆቹና ጉልበቱ እንደሚዳኸው እንሱም እየዳኹ ይመጡ እንደነበር ተናገሩ። _ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ኢቃም እንድትባል አዘው በሳቸው ምትክ አንድ የሚያሰግድ ሰው ሊመድቡና ከዚያም የታሰረ እንጨት ከተሸከሙ ሰዎች ጋር በመሆን ጀመዓ ሶላት ወደማይገኙ ወንዶች ሂደው ጀመዓ ባለመገኘት የሰሩት ወንጀል ከባድ ስለሆነ ቤታቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ቆርጠው ነበር። ነገር ግን ቤት ውስጥ ንፁህ ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎችም የሚያስቀር ምክንያት ያላቸው ስላሉ አላደረጉትም።فوائد الحديث
ሶላተል ጀመዓን በመስጊድ ከመስገድ የመራቅ አደገኝነትን እንረዳለን።
ሙናፊቆች በአምልኳቸው ይዩልኝና ይስሙልኝ በስተቀር ሌላ ምንም አያስቡም። ሰዎች በሚያያቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር ወደ ሶላት አይመጡም።
ከጀመዓ ጋር ዒሻና ፈጅርን የመስገድ ምንዳ ትልቅነቱን እንረዳለን። እየዳኹ እንኳ ቢሆን ወደነሱ መምጣት የተገባ ነው።
ዒሻና ፈጅር በመስገድ ላይ መጠባበቅ ከንፍቅና መንፃት መሆኑን ከነርሱ መቅረት ደግሞ የሙናፊቆች ባህሪ መሆኑን እንረዳለን።