'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'

'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'

ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞችና በሌሎች ከሀዲያንና መናፍቃን መካከል ያለው መተማመኛና ቃል ኪዳን ሶላት እንደሆነና ሶላትን የተወ ሰውም በርግጥ እንደካደ ገለፁ።

فوائد الحديث

የሶላት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነና በአማኝና በከሀዲ መካከል መለያም እንደሆነ እንረዳለን።

የሙስሊምነት ፍርድ በሰውዬው ውስጣዊ ማንነት ላይ ሳይሆን ውጫዊ ማንነቱ ላይ በመንተራስ እንደሚፀና።

التصنيفات

ኢስላምን የሚያፈርሱ ነገሮች, ክህደት (ኩፍር), የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ