እውነቱን ከተናገረ ስኬታማ ሆነ!" አሉ።

እውነቱን ከተናገረ ስኬታማ ሆነ!" አሉ።

ከጦልሓ ቢን ዑበይዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ፀጉሩ የተበታተነ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ፤ ወደ አላህ መልእክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስኪቀርቡ ድረስ ከፍ ያለ ድምፁን እንሰማ ነበር ነገር ግን የሚናገረውን ልንረዳው አልቻልንም፤ ለካ ስለ እስልምና እየጠየቀ ኖሯል። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲመልሱለት "በቀንና በምሽት የሚሰገድ አምስት ሶላቶች ነው።" አሉት። እርሱም "ከነዚህ ሶላቶች በቀር ሌላ ሶላት አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምተሰግደው ሶላት) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም። እንዲሁም የረመዳንን ወር መጾም።" አሉት። እርሱም "ከዚህ ጾም በቀር ሌላ ጾም አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፍቃደኝነት (የምትጾመው ጾም) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካንም አወሱለት። እርሱም "ከዚህ ውጪ ሌላ የምፅዋት ግዴታ አለብኝን?" አላቸው። እርሳቸውም "አይ በፈቃደኝነት (የምትመፀውተው) ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም።" አሉት። ሰውዬውም "በአላህ እምላለሁ! ከዚህ አልጨምርምም አልቀንስምም።" እያለ ዞሮ ሄደ። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እውነቱን ከተናገረ ስኬታማ ሆነ!" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ፀጉሩ የተበታተነ፣ ድምፁ ከፍ ያለ፣ የሚናገረው የማይገባ የነጅድ ነዋሪ የሆነ ሰው ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣ። ወደነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀረበና ስለ እስልምና ግዴታዎችም ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶላት ጀመሩና አላህ በሁሉም ቀንና ምሽቶች አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገበት ነገሩት። እርሱም: ከነዚህ አምስት ሶላቶች በቀር ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: ሱና ሶላቶችን በፈቃደኝነት ልትሰግድ ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው እንዲህ አሉት: በአንተ ላይ አላህ ግዴታ ካደረገብህ ነገሮች መካከል የረመዳንን ወር መጾም አንዱ ነው። ሰውዬውም "ከረመዳን ጾም ውጪ ሌላ ጾም መጾም ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ?" አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልጾምክ በቀር የለብህም አሉት። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘካን አወሱለት። ሰውዬውም: የግዴታ ዘካዬን ካወጣሁ በኋላ ሌላ ምፅዋት ግዴታ ይሆንብኛል እንዴ? አላቸው። እርሳቸውም: በፈቃደኝነት ካልሆነ በቀር ሌላ የለብህም አሉት። ሰውዬው እነዚህን ግዴታዎች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሰማ በኋላ ከእነሱ ምንም ሳይጨምርና ሳይቀንስ ዘውትሮ እንደሚተገብር በአላህ ምሎ እየተናገረ ዞሮ ሄደ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ይስፈንና ይህን አስከትለው ሰውዬው የማለበትን ነገር የእውነት ከፈፀመ ከሚድኑት ሰዎች ይሆናል አሉ።

فوائد الحديث

የእስልምና ድንጋጌዎች ትእዛዙ በሚመለከታቸው ሰዎች ላይ ገርና ቀላል መሆኑን እንረዳለን።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰውዬው ቀርቧቸው እንዲጠይቃቸው ራሳቸውን በማስመቸታቸው ከዚህ ሰውዬ ጋር የነበራቸውን መልካም ግብረ ገብነት እንረዳለን።

ወደ አላህ በምናደርገው ጥሪ እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ጉዳይ መጀመር እንዳለብን እንረዳለን።

እስልምና የእምነት ብቻ ሳይሆን የተግባርም ሃይማኖት ነው። ያለ እምነት ስራ ምንም አይጠቅምም፤ እምነትም ያለስራ አይጠቅምም።

እነዚህ ተግባራት አንገብጋቢና የእስልምናም ማዕዘን እንደሆኑ እንረዳለን።

ሶላት ግዴታ በሆነበት ሰው ላይ በዙህር ሶላት ምትክ ስለሆነች የጁሙዓ ሶላትም ግዴታ ከሆኑት አምስቱ ሶላቶች ውስጥ ይካተታል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስተምህሮታቸውን ከእስልምና ግዴታዎች መካከል እጅግ ጠንካራ በሆነው ጀመሩ። እርሱም ከሁለቱ ምስክሮች ቀጥሎ ያሉት ማዕዘናት ናቸው። ከሸሀዳ ያልጀመሩት ሙስሊም ስለነበር ነው። ሐጅን ያልጠቀሱለት ደግሞ ግዴታ ከመደረጉ በፊት ስለሆነ ወይም ወቅቱ የሐጅ ወቅት ስላልነበር ነው።

አንድ ሰው በሸሪዓ ግዴታዎቹን በመወጣት ላይ ብቻ ከተቆጠበ ይድናል። ነገር ግን ይህ ማለት ሱና ነገሮችን መፈፀሙ አልተደነገገም ማለት አይደለም። ሱና ስራዎች የትንሳኤ ቀን ግዴታዎችን ይሞላሉና።

التصنيفات

ኢስላም