በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።

በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።

ጃቢር ቢን ዐብደሏህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "በአሏህ ሳያጋራ አሏህን የተገናኘ ጀነት ገብቷል፤ እያጋራበት አሏህን የተገናኘ ደግሞ እሳት ገብቷል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በአሏህ ላይ አንዳችም ሳያጋራ የሞተ በተወሰነ ወንጀሉ ተቀጥቶም ቢሆን መመለሻው ወደ ጀነት መሆኑን፤ በአሏህ ላይ አንዳችም አጋርቶ የሞተ ደግሞ ጀሀነም መዘውተሪያው መሆኑን ተናገሩ።

فوائد الحديث

ተውሒድ ያለው ትሩፋት፤ በእሳት ውስጥ ከመዘውተር ለመዳንም ሰበብ መሆኑን፤

የሰው ልጅ ከጀሀነምም ይሁን ከጀነት ጋር ያለው ቅርበት፤ በእነርሱና በሰውየው መካከል ያለውም ሞት ብቻ መሆኑን፤

ከጥቂትም ይሁን ከብዙ ሽርክ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤ ምክንያቱም ከጀሀነም እሳት መዳን የሚቻለው ያንን በመራቅ ስለሆነ፤

ስራዎች ዋጋ የሚሰጣቸው በፍፃሜያቸው መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ማጋራት (ሺርክ), የጀነትና እሳት ባህሪዎች