በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው።

በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ((የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው። ከአንዳች ነገር የከለከልኳችሁ ጊዜ ራቁት፤ በአንድ ትእዛዝ ያዘዝኳችሁ ጊዜ ደሞ የቻላችሁትን ያህል ከርሱ ፈፅሙ!"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሸሪዓ ድንጋጌዎች ለሶስት እንደሚከፈሉ ገለፁ። እነሱም: ዝም የተባለ፣ ክልከላዎችና ትእዛዛት ናቸው። የመጀመሪያው: አላህና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለርሱ ዝም ያሉት ነው። ፍርድ ከሌለው የነገሮች መሰረቱ ግዴታ አለመሆኑ ነው። በርሳቸው ዘመን ስለአንዳች ስላልተከሰተ ነገር መጠየቅን መተው ግዴታ ነበር። ይህም በርሳቸው ላይ ግዴታ የሚያደርግ ወይም ክልክል የሚያደርግ መመርያ እንዳይወርድ ነው። አላህ የተዋት ለባሮቹ በማዘኑ ነውና። እርሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሞቱ በኋላ ግን ጥያቄው ፈታዋ በመጠየቅ መልኩ ወይም በሃይማኖቱ ጉዳይ የሚያስፈልገውን በመማር መልኩ የቀረበ ከሆነ ይህ የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘበትም ጭምር ነው። ጥያቄን ተጨንቆ ፈጥሮና በግትርነት ከሆነ የጠየቀው ግን እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መጠየቅን በመተው የተፈለገው ይህ አይነቱን ነው። ይህም በኒ ኢስራኤሎች ላይ የተከሰተው አምሳያ ወደመከሰት ስለሚያመራ ነው። ይህም ላም እንዲያርዱ በታዘዙ ወቅት ማንኛውንም የላም አይነት ቢያርዱ ትእዛዙን እንደፈፀሙ ይቆጠርላቸው ነበር። ነገር ግን እነሱ በመጠየቅ ሲያጠብቁት ትእዛዙም ጠበቀባቸው። ሁለተኛው: ክልከላዎች ናቸው: ይህም መተዉ የሚያስመነዳ መተግበሩ የሚያስቀጣ ነው። ይህንንም ሙሉ ለሙሉ መራቅ ግዴታ ነው። ሶስተኛው: ትእዛዝ ነው። እርሱም መስራቱ የሚያስመነዳ መተዉ የሚያስቀጣ ነው። በአቅም ልክ መተግበሩም ግዴታ ነው።

فوائد الحديث

አስፈላጊና አንገብጋቢ በሆነ ነገር ላይ መጠመድ ተገቢ ነው። ለጊዜው አስፈላጊ ያልሆነን ነገር መተውና ያልተከሰተን ነገር በመጠየቅ ከመጠመድ መታቀብም ተገቢ ነው።

ምናልባትም ጉዳዮችን ወደ መወሳሰብ የሚያደርስና ልዩነት እንዲበዛ መንስኤ የሚሆን የውዥንብርን በር የሚከፍት ጥያቄ መጠየቅ ክልክል ነው።

ሁሉንም ክልከላዎች በመተው መታዘዙ። ምክንያቱም መተዉ ምንም ስለማይከብድ ነው። ስለዚህም ነው ክልከላው አጠቃላይ የሆነው።

ትእዛዛትን መፈፀም ከአቅምና ችሎታ ጋር የተቆራኘ መሆኑን እንረዳለን። ይህም አንዳንዴ ትእዛዝን መፈፀም ሊከብድ ወይም አለመቻል ሊገጥም ይሆናል። ስለዚህም ትእዛዝን መፈፀም የታዘዘው ከአቅም ጋር ተቆራኝቶ ሆነ።

ጥያቄን ማብዛት መከልከሉን እንረዳለን። ዑለማዎች መጠየቅን ለሁለት ከፍለውታል: አንደኛው: የሚያስፈልገውን ሃይማኖታዊ ጉዳይ በመማር መልኩ መጠየቅ ነው። በዚህ አላማ መጠየቅ ታዟል። የሶሐቦችም ጥያቄ በዚህ መልኩ ነበር። ሁለተኛው: ጥያቄን በመጨነቅና በግትርነት መልኩ መጠየቅ ሲሆን ይህኛው ግን የተከለከለው የመጠየቅ አይነት ነው።

ይህ ኡማ ከዚህ በፊት የነበሩት ህዝቦች ነቢያቸውን እንደተቃረኑት ነቢያቸውን ከመቃረን መከልከላቸውን እንረዳለን።

የማያስፈልግ ጥያቄ ማብዛትና ነቢያቶችን መቃረን የጥፋት ሰበብ ነው። በተለይ መልሱ የማይደረስበትን ጥያቄ መጠየቅ ለምሳሌ: ከአላህ በቀር ማንም የማያውቃቸውን የሩቅ እውቀት፣ የትንሳኤ ቀንን ሁኔታዎች መጠየቅ ይገኙበታል።

ከባባድ ርዕሶችን ከመጠየቅ መከልከሉ። አውዛዒ እንዲህ ብለዋል: "አላህ የእውቀትን በረከት ባሪያውን ሊነፍገው የፈለገ ጊዜ ምላሱ ላይ ጥያቄ ማብዛትን ይጥልበታል። እንደዚ አይነት ሰዎችን ትንሽ እውቀት ያላቸው ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።" ኢብኑ ወህብ እንዲህ ብለዋል: ማሊክ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "እውቀትን መከራከር ከሰውዬው ቀልብ ውስጥ የእውቀትን ብርሀን ያስወግዳል።"

التصنيفات

ቀዳሚ መልክተኞችና ነቢያቶች የአላህ ሰላም ይስፈንባቸው።, የቃላቶች ጥቆማና እውቀትን የማውጣት (የኢስቲንባጥ) ሁኔታ