አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ በአልጋው ላይ ወደተደገፈ አንድ ሰውዬ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው

አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ በአልጋው ላይ ወደተደገፈ አንድ ሰውዬ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው

አልሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፡- “የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡- "አዋጅ! ከእኔ የሆነ ሐዲሥ በአልጋው ላይ ወደተደገፈ አንድ ሰውዬ ይደርሰውና፡ "በእኛና በእናንተ መካከል (የሚዳኘን) የአላህ መጽሐፍ ነው። በውስጡ የተፈቀደ ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐላል እንቆጥረዋለን በውስጡም ሐራም ሆኖ ያገኘነውን (ብቻ) እንደ ሐራም እንቆጥረዋለን።" የሚልበት ወቅት ቅርብ ነው። በእርግጥ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐራም (እርም) ያደረጉት ማንኛውም ነገር አላህ ሐራም እንዳደረገው ነው።'”

[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሰዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች አንድ ፍራሹ ላይ የተደገፈ ሰው፥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐዲሥ ሲደርሰው "በጉዳዮቻችን ላይ በእኛና በናንተ መካከል የሚዳኘን የተከበረው ቁርኣን ነው፤ እሱ በቂያችን ነው፤ በቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐላሎች (ፍቁድ) እንሰራበታለን፤ ቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐራሞች (እርሞች) እንርቀዋለን። " የሚልበት ዘመን እንደቀረበ ተናገሩ። ቀጥለው ሁሉም በሱናቸው (ሀዲሳቸው) እርም ያደረጉት ወይም የከለከሉት ነገር ደረጃው ልክ አላህ በቁርኣኑ እንደከለከለው አምሳያ እንደሆነ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አብራሩ። ምክንያቱም እሳቸው የጌታቸውን መልዕክት አድራሽ ናቸውና።

فوائد الحديث

ቁርኣን እንደሚከበረውና ከሱ ድንጋጌዎች እንደሚወሰደው ሁሉ ሱናንም ማላቅ እንደሚገባ እንረዳለን።

መልክተኛውን መታዘዝ አላህን መታዘዝ ነው፤ እሳቸውንም አለመታዘዝ አላህን አለመታዘዝ ነው።

የሐዲሥ ማስረጃነት የፀና መሆኑና ሐዲሥን የማይቀበል ወይም የሚያወግዝ ሰው ላይ በቂ ምላሽ መሰጠቱን እንረዳለን።

ከሐዲሥ በማፈንገጥ በቁርኣን ብቻ መብቃቃትን የሞገተ ሰው፥ በሁለቱም ላይ ያፈነገጠና ቁርኣንን እከተላለሁ የሚለው ሙግቱም ቅጥፈት እንደሆነ ያስረዳል።

የነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነቢይነት ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል ለወደፊት ይከሰታል ብለው የተናገሩት ነገር እንደተናገሩት መከሰቱ ነው።

التصنيفات

የሱና አንገብጋቢነትና ያለው ደረጃ, ነቢይነት, የቀብር (የበርዘኽ) ህይወት