አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን

አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን

ከኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዐዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን በሚልኩበት ጊዜ እንዲህ አሉት፡ ' አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ወደ መመስከር ጥሪ አድርግላቸው። እነሱ ለዚህ ጥሪህ ታዛዥ ከሆኑ አሏህ በነሱ ላይ በቀንና ምሽቱ ሁሉ አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዥ ከሆኑ አላህ በነሱ ላይ ከሀብታሞቻቸው ተይዞ ወደ ድሆቻቸው የምትሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዦች ከሆኑ አደራህን ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) ተጠንቀቅ! የተበዳይንም ልመና ተጠንቀቅ! እነሆ በሷና በአላህ መሀል ግርዶሽ የለምና።'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዐዝ ቢን ጀበልን - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ወደ አላህ መንገድ ተጣሪና አስተማሪ በማድረግ ወደ የመን በላኩበት ወቅት ከክርስቲያን የሆኑ ህዝቦችን ስለሚጋፈጥ እነርሱን በተመለከተ ዝግጁ እንዲሆን አሳሰቡት። ቀጥለውም ዳዕዋውን እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ነጥብ እንዲጀምር ነገሩት። መጀመርያ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ብለው በአሏህ አንድነትና በሙሐመድ መልዕክተኝነት በመመስከር እምነታቸውን እንዲያስተካክሉ ጥሪ እንዲያደርግ፤ ምክንያቱም ወደ እስልምና የሚገቡት በዚህ የምስክርነት ቃል ስለሆነ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ካደረጉ ሶላትን እንዲሰግዱ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ምክንያቱም ከተውሒድ በኋላ ትልቁ ግዴታ ይህ በመሆኑ ነው። ሶላትንም ካስተካከሉ በኋላ ከመካከላቸው ያሉት ባለ ፀጎች በመካከላቸው ላሉት ድሆች ከገንዘባቸው ዘካን እንዲያወጡ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለዘካ ብሎ ከውድ ንብረታቸው እንዳይወስድ አስጠነቀቁት። ምክንያቱም የመስጠት ግዴታቸው ከመካከለኛ ንብረታቸው ነውና። ከዚያም የተበዳይ ዱዓእ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተበዳይ ዱዓእ እንዳያደርግበት ግፍን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰቡት።

فوائد الحديث

በ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" የመመስከር ትርጉም አሏህን በአምልኮ መነጠልና ከአሏህ ውጭ ምንንም አለማምለክ እንደሆነ፤

ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን የመመስከር ትርጉሙ በሳቸውም ማመን፣ ይዘውት በመጡትም እውነትነቱን ማመን፤ እሳቸው ወደ ሰው ልጆች ከተላኩት የመጨረሻው መልዕክተኛ መሆናቸውንም ማመን መሆኑን፤

የእውቀት ባለቤት ወይም እርሱ ዘንድ ማምታቻ ያለውን ሰው ማናገር መሀይምን እንደማናገር አለመሆኑን፤ ስለዚህም ነው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዓዝን እንዲህ በማለት የጠቆሙት፡ "አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ።"

ሙስሊም በዲኑ ጉዳይ አወዛጋቢዎች ከሚያመጡት ማምታቻ መጥራት እንዲችል በእውቀት ላይ ሊሆን እንደሚገባው፤ ይህም ዒልም በመፈለግ የሚሆን ነገር ነው።

የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከተላኩ በኋላ የአይሁዶችና የክርስያኖች ሃይማኖት ውድቅ መሆኑን፤ በነቢያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምነው ወደ እስልምና እስካልገቡ ድረስም ከሚድኑት ጎራ አለመሆናቸውን እንረዳለን።

التصنيفات

ኢስላም