إعدادات العرض
የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ…
የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'
ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"
[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių தமிழ் Wolof Українська Shqip ქართული Moore Magyarالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከሒሳብ መተሳሰቢያ ስፍራ አንድም ሰው ስለተወሰኑ ጉዳዮች ሳይጠየቅ ወደ ጀነት ወይም ወደ እሳት እንደማያልፍ ተናገሩ። የመጀመሪያው: ህይወቱን በምን እንዳጠፋውና እንዳሳለፈው? ሁለተኛው: ዕውቀቱን ለአላህ ብሎ ነው የፈለገው? በእውቀቱ ሰርቶበታልን? ማወቅ ለሚገባውስ አስተላልፎታልን? ሶስተኛው: ገንዘቡን ከየት ነው ያገኘው? ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም? ለምንስ አዋለው? አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ አዋለው? ወይስ በሚያስቆጣው ነገር ላይ? አራተኛው: ስለ አካሉ፣ ሀይሉ፣ ጤንነቱ፣ ወጣትነቱ ነው። ምን ላይ ተጠቅሞ እንዳሳለፈው?فوائد الحديث
ህይወትን ማሳለፍ ያለብን አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ እንዲሆን መነሳሳቱን እንረዳለን።
አላህ በባሮቹ ላይ የዋለው ፀጋ ብዙ ናቸው። ስለነበረበት ፀጋም ይጠይቀዋል። ስለዚህ የአላህን ፀጋዎች እርሱን በሚያስደስት ነገር ላይ ማዋል ይገባዋል።
التصنيفات
የመጨረሻው ህይወት