ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።

ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱው ይመደባል።"

[ሐሰን ነው።] [አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

የነርሱ መለዮ የሆነን እምነት ወይም አምልኮ ወይም ተለምዷዊ ነገርን በማድረግ ከከሀዲያን ወይም ከአመፀኞች ወይም ከደጋግ ህዝቦችም ጋር የተመሳሰለ ሰው ከነርሱ እንደሚመደብ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። ምክንያቱም በውጫዊ ማንነት ከነርሱ ጋር መመሳሰል በውስጣዊ ማንነት ከነርሱ ጋር ወደ መመሳሰል ያደርሳልና። ከሆኑ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በነሱ የመደነቅ ውጤት መሆኑ ጥርጥር የሌለው ጉዳይ ነው። ቀስ በቀስም እነሱን ወደመውደድ ፣ ወደማላቅ፣ ወደነርሱ ጥገኛ ወደመሆን ያደርሳል። ይህም አላህ ይጠብቀንና ሰውዬውን በውስጣዊ አመለካከቱና አምልኮው ሳይቀር ከነርሱ ጋር ወደመመሳሰል ይጎትተዋል።

فوائد الحديث

ከከሀዲያንና አመፀኛ ህዝቦች ጋር መመሳሰል መከልከሉን ፤

ከደጋጎች ጋር መመሳሰልና እነሱን መከተል መበረታታቱን ፤

በውጫዊ ማንነት መመሳሰል በውስጥ መውደድን እንደሚያወርስ ፤

ሰውዬው በተመሳሰለው ልክና አይነት ወንጀልና ዛቻ እንደሚያጋጥመው ፤

ከከሀዲያን ጋር እነሱ የተለዩበት በሆኑ እምነታቸውና ተለምዷቸው መመሳሰል መከልከሉን እንረዳለን። ይህ ባልሆነበት የተለያዩ ሙያዎችን መማርና የመሳሰሉት ግን ክልከላው ውስጥ አይካተትም።

التصنيفات

የተከለከለው መመሳሰል