إعدادات العرض
አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል።
አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንድም ነቢይ ለህዝቦቹ ያልተናገረውን ስለደጃል አንድ ነገር አልነግራችሁምን? እርሱ እውር ነው፣ እርሱ ጀነትና እሳት በሚመስል ነገር ከራሱ ጋር ይዞ ይመጣል። እርሷ ጀነት ናት የሚላት እሳት ናት። እኔ ኑሕም ህዝቦቹን እንዳስጠነቀቀው አስጠነቅቃችኋለሁ።"»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල دری অসমীয়া ไทย Tiếng Việt Svenska Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી नेपाली Oromoo മലയാളം Română Nederlands Soomaali پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Malagasyالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረቦቻቸው ስለደጃል፣ ስለባህሪያቱና ምልክቶቹ ከርሳቸው በፊት ማንም ነቢይ ያልተናገረውን ነገሯቸው። ከዚህም መካከል:- እርሱ አንድ‐ዓይና ነው። አላህ ከርሱ ጋር ለዓይን በሚታይ መልኩ ጀነትና እሳት የሚመስልን ነገር እንዳደረገለት፤ ነገር ግን ጀነት መስሎ የሚታየው እሳት፣ እሳት መስሎ የሚታየው ጀነት ነው። እርሱን የታዘዘን ለሰው "ጀነት" መስሎ በሚታየው ውስጥ ይከተዋል። ነገር ግን እርሷ የምታቃጥል እሳት ናት። እርሱን ያመፀን ለሰው "እሳት" መስሎ በሚታየው ውስጥ ይከተዋል። ነገር ግን እርሷ ምርጥ ጀነት ናት። ቀጥለውም ልክ ኑሕ ለህዝቦቹ እንዳስጠነቀቀው ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከደጃል ፈተና አስጠነቀቁን።فوائد الحديث
የደጃል ፈተና ትልቅነትን እንረዳለን።
ከደጃል ፈተና መዳን በእውነተኛ ኢማን፣ ወደ አላህ በመጠጋት፣ በመጨረሻው ተሸሁድ ወቅት ከርሱ በአላህ በመጠበቅና ከሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን በመሸምደድ ይገኛል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው በፊት ያለ ማንም ነቢይ ያላብራራውን የደጃል ባህሪያት ለሙስሊሞች ማብራራታቸው ለኡመታቸው መመራት ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት ያስረዳናል።