ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም።

ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም።

ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አንድ ምሽት ላይ ሶሐቦች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበሩ። የ14ኛዋን ምሽት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: አማኞች ጌታቸውን ያለምንም ጥርጥር በዓይኖቻቸው በእውነት ያዩታል። የበላይ የሆነውን አላህ በሚያዩት ወቅት ምንም አይገፋፉምም፣ ልፋትና ችግርም አያገኛቸውም። ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ከፈጅር ሶላትና ከዐስር ሶላት የሚከለክሏችሁን ምክንያቶች መግታት ከቻላችሁ አድርጉት። ሁለቱንም ሶላቶች በወቅታቸው በህብረት በተሟላ መልኩ ፈፅሙ። ይህ ወደ አላህ ፊት ለመመልከት ከምክንያቶች መካከል አንዱ ነውና። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺን አንቀፅ አነበቡ: {ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}

فوائد الحديث

የኢማን ባለቤቶች ጀነት ውስጥ አላህን እንደሚመለከቱት ብስራት እንዳላቸው እንረዳለን።

ከዳዕዋ መንገዶች መካከል: ጉዳይን ማጠንከር፣ ማነሳሳትና ምሳሌን መጥቀስ ጥቂቶቹ ናቸው።

التصنيفات

የመጨረሻው ህይወት