አላህ ለርሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።

አላህ ለርሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ለርሱ መልካም የሻለትን ሰው ይፈትነዋል።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

አላህ በአንድ አማኝ ባሪያው ላይ መልካምን የፈለገ ጊዜ በነፍሳቸው፤ በገንዘባቸውና በቤተሰቦቻቸው እንደሚፈትናቸው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተናገሩ። ይህም አንድ አማኝ በሱ ምክንያት ወደ አላህ በዱዓእ መጠጋት፣ የወንጀል መማርና የደረጃ ከፍ ማለትን ስለሚያገኝ ነው።

فوائد الحديث

አማኝ የሆነ ሰው ለተለያዩ የመከራ አይነቶች የተጋለጠ ነው።

ፈተና የአንድ አማኝን ደረጃ ከፍ ከማድረጉ፣ ማዕረጉን ከመስቀሉና ወንጀሉን ከማስማሩ አኳያ አላህ ለባሪያው ላለው ውዴታ ምልክት ሊሆን ይችላል።

በመከራዎች ላይ ትእግስት በማድረግና ባለመበሳጨት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።

التصنيفات

የቀዷና ቀደር ጉዳዮች