ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።

ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዷን ተናገሩ እኔ ደግሞ ሌላዋን ተናገርኩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ‹ ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።› እኔ ደግሞ: ‹ለአላህ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) ሳይጣራ የሞተ ሰው ጀነት ይገባል።› አልኩኝ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ያለን አካል መጣራትና ከአላህ ውጪ ካለ አካል እርዳታ መፈለግን የመሰለ ለአላህ ሊደረግ ግዴታ የሆነን አንዳች ነገር ለሌላ እየሰጠ የሞተ ሰው የእሳት ባለቤት መሆኑን ነገሩን። ኢብኑ መስዑድም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በአላህ አንዳችን ሳያጋራ የሞተ ሰው መመለሻው ወደ ጀነት ነው የሚለውን ጨመሩ።

فوائد الحديث

ዱዓእ ለአላህ ካልሆነ በስተቀር የማይሰጥ አምልኮ ነው።

በተውሒድ ላይ የሞተ ሰው በከፊል ወንጀሉ ቢቀጣም እንኳ ጀነት መግባቱ የተውሒድን ትሩፋት ያስረዳናል።

በሺርክ ላይ የሞተ ሰው እሳት መግባቱ የሺርክን አደገኝነት ይጠቁማል።

التصنيفات

አላህን በተመላኪነቱ መነጠል